Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address በጉራጌ ዞን ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0967441304
  • Website
  • Deadline01 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security44,000 (አርባ አራት ሺህ ብር)
  • opening date2025-12-01 00:00:00
  • Categories Construction Works

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት አመት በተያዘው ካፒታል በጀት በወረዳው ከተማ ቋንጤ ውስጥ ሞዴል ቅድመ መደበኛ የመማሪያ ክፍል ለማስገንባት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ጌ/ወ/ፋ/ግ/ጨ/መ/ቁ/02/2018

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት አመት በተያዘው ካፒታል በጀት በወረዳው ከተማ ቋንጤ ውስጥ ሞዴል ቅድመ መደበኛ የመማሪያ ክፍል ለማስገንባት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት በሙሉ የምታሟሉ ማንኛውም ተጫራቶች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን

  1. የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ አቅራቢዎች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በጣት አሻራ ላይ የተመሰረተ እና የተረጋገጠ መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  2. የቫት ተመዝጋቢ የሆናችሁ።
  3. ተጫራቾች በግንባታ ስራ ተቋራጭ በደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑና የዘመኑ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የተሰጠ ማስረጃና የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች በግንባታ ስራ በአቅራቢነት የተመዘገቡ እና ስለ መመዝገባቸው የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  5. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውከልና ይዘው መቅረብ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የብቃት ማረጋገጫ የታደሰ የበጀት ዓመቱ ማቅረብ የምትችሉ መሆን አለባቸው።
  7. ተጫራቾች በግንባታ ስራ በአቅራቢነት በኦን ላየን ብቻ የተመዘገቡ እና ስለ መመዝገባቸው የሚገልጽ መረጃ ሰርተፊኬት e-GP /Electronic Government procurement ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  8. የ2018 በጀት አመት ከግብር ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ (Tax Clearance for 2018 E.C)
  9. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደ ሚሆኑ ለወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ይሆናል።
  10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ በግልጽ ጽሁፍ የተጠየቀውን መረጃ ብቻ በአግባቡ የሚያቀርቡ እና ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን አለበት ስርዝ ቢፈጠር በተፈጠረው ቦታ ፊርማ የማኖር ግደታ መሆኑን መረዳት ይጠበቃል።
  11. ተጫራቾች የጨረታው ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመት ሲያቀርቡ፡-

ሀ. ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸው በጥንቃቄ በታሸገ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ ቴክኒካል በሚል በመለየት በድርጅቱ ባለስልጣን ተፈርሞበት እና ማህተም የተደረገበት መሆን አለበት፡፡

ለ. ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸው በጥንቃቄ በታሸገ በድርጅቱ ባለስልጣን በእያንዳንዱ ገጽ የተፈረመበት እና ማህተም የተደረገበት ሆኖ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ (ፋይናንሻል በሚል በመለየት እስከ 21ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ጌታ ወረዳ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

  1. ተጫራቾች የግንባታ ስራው የሚሰራበት ቦታ በአካል በማየት ስለ ማየታቸው ከት/ት/ጽ/ቤት የተወከለ አካል የተፈረመበት እና የት/ት/ጽ/ቤቱ ማተህም የተደረገበት መረጃ በመቀበል በቴክኒካል ሰነዱ መጨመር ግዴታ ይሆናል ይህንን የቦታ ምልከታ ያላያያዘ ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይደረጋል።
  2. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይንም ከጨረታ እራስን ማግለል አይቻልም፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 44,000 (አርባ አራት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO (በካሽ) ወይም ከመድን ድርጅቶች የሚቀርብ ዋስትና በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረት ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ቦንድ በጌታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከኦሪጅናል ቴክኒካል ዶክመንት ጋር በማድረግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ ቴክኒካል በሚል በመለየት በድርጅቱ ባለስልጣን ተፈርሞበት እና ማህተም የተደረገበት መሆን አለበት።
  4. ግዥ ፈጻሚ አካል አሸናፊ ከተለየ በኋላ በሚገዛቸው የግንባታ ስራዎች 20% ፐርሰንት የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት ይኖረዋል።
  5. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ጥያቄ ለግዥ ፈጻሚ አካል ማቅረብ የሚችሎት ጨረታው ከመከፈቻ 5 ቀናት በፊት በጽሁፍ መሆን አለበት።
  6. በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በግንባታ የስራ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ጨረታው ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በተከታታይ እስከ 21ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ የጌታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት ማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይቻላል።
  7. የጨረታ ሳጥኑ 21 /ሃያ አንደኛ/ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 8፡00 ሰአት በጨረታው ኮሚቴ ታሽጎ በዚያው እለት 8፡30 ተጫራቾች /ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል /ባይገኙም ይከፈታል።

ማሳሰቢያ

  1. ግዢ ፈጻሚው አካል ጨረታው በሙሉም (በከፊል) የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፤
  2. በአፈጻጸም ምክንያት ከዚህ በፊት በወረዳው ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ተቋራጮች መወዳደር አይችሉም
  3. ማንኛውም ተጫራች ለቴክኒካል ዶክመንት የተጠየቀውን መረጃ ብቻ ግልጽ እና በማያሻማ መልኩ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
  4. የቫት 7.5% የምንቆርጥ መሆኑን እናሳስባለን።

ተጫራቾች ዋጋ ስትሞሉ ቫትን ባካተተ ሁኔታ መሙላት ይጠበቅባችኋል ካልሆነ ቫት እንደ ተካተተ ተቆጥሮ ይወሰዳል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር /0961178110/0967441304/0925838193 መደወል ይችላሉ፡፡

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት

 

Save Tender