Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ
  • Address በጉራጌ ዞን : በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113659158
  • Website
  • Deadline24 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • opening date2025-11-24 00:00:00
  • Categories Construction Works

በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ በ2018 ዓ.ም በኮዋሽ ፕሮጀክት ድጋፍ በአበሽጌ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት የጣጤሳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ የሆሌ ሚሊኒየም 1ኛ ደረጃ ት/ቤት እና የቱሉላሜ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የመጸዳጃ ቤት ግንባታዎች ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ በ2018 ዓ.ም በኮዋሽ ፕሮጀክት ድጋፍ በአበሽጌ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት የጣጤሳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ የሆሌ ሚሊኒየም 1ኛ ደረጃ ት/ቤት እና የቱሉላሜ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የመጸዳጃ ቤት ግንባታዎች ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ ዶክሜንታቸውን ዋናውንና አንድ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። በጨረታው ለሚወዳደሩ ተጫራቾች ፈቃዳቸው BC/GC ደረጃ 5 (አምስት) እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው። በዘርፉ የ2018 ዓ.ም. የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የግንባታ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደስ የብቃት ማረጋገጫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ጊዜው ያላለፈበት ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ እና የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በአበሽጌ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ማ/ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ መውሰድ ይችላሉ። ማንኛውም ተጫራች ለ60 (ስልሳ) ቀናት የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / BID BOND / 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ የማቅረብ ግዴታ አለበት። የቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መቅረብ ያለበት በቴክኒካል ኦርጂናል ሰነድ ውስጥ ወይም ከፖስታው ውጪ በእጅ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ቴከኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ፣ ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ አርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም በሰም የታሸጉትን 6 ፖስታዎች በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማድረግ የድርጅቱን ማህተም እና ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። እንዲሁም የጨረታው ፋይናንሻል ሰነድ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የተስተካከለ ከሆነ ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል። ተጫራቾች የሥራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ መወዳደሪያ ላይ ስማቸው፣ ፊርማቸው፣ አድራሻቸው፣ ማህተም በማድረግ እና ኢንቨሎፑን በሰም በማሸግ የጨረታ ማስታወቂያው በወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን በአበሽጌ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ማ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 8:00 ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው የሥራ ቀን በእለቱ ባለቤቱ ወይንም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በፋ/ኢ/ል/ማ/ጽ/ቤት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በዕለቱ 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል። የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል። ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0113659378 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

 

በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ

 

Save Tender