Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ፌደሬሽን
  • Address ሀዋሳ ከተማ ሞሀ የለስላሳ መጠቶች ፋብሪካ አጠገብ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462214837
  • Website
  • Deadline10 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Security50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • opening date2025-11-10 00:00:00
  • Categories Agriculture And Farming , Flora And Horticulture

የደቡብ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ፈዴሬሽን ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ የተለያዩ የጓሮ አትክልት ዘሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የደቡብ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ፌደሬሽን


 

በድጋሚ የወጣ የጓሮ አትክልት ዘር ግዥ

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር፡- 002/2018

 

የደቡብ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ፈዴሬሽን ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ የተለያዩ የጓሮ አትክልት ዘሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆንም ተጫራቾች እያንዳንዱን የጓሮ አትክልት ዘር አንዱን ኪሎ ግራም በስንት ብር ሊሸጡ እንዲችሉ የመወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

  1. በዘርፉ ሕጋዊ አስመጪነት የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤
  2. ከሚመለከተው ክፍል የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. ተጫራቾች ዘሩን ወደ ሃገር ውስጥ ሲያስገቡ ከኢፌዲሪ ግብርና ሚኒስቴር የተሰጣቸውን የብቅለት እንዲሁም የጥራት ማረጋገጫ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. የጨረታ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ /CPO/ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጓሮ አትክልት ዘር የዝርያውን ዓይነት በተመለከተ፡-
  • የቀይ ሽንኩርት ዝርያ ሬድ ቦምቤ፣ ሬድ ክሮይል፣ ሬድ ኪንግ፣ ኒፍቶን፣ ሩሴት፣ ሆላንድ፣ ሲሪያል፤
  • የቲማቲም ዝርያ ሮማ ቪኤፍ፣ ገሊሊያ፣ ቬነስ፣ ቫርነም፤ ኮምቶ፣ ምንካ፣ ሻንቲ፣ ማርግሎቭ፤
  • የጥቅል ጎመን ዝርያ ኮገንሀገን፣ ቫንደግ፣ ዩሮ ቪክቶሪያ፣ ላንዳኒ፣
  • የተዳቀሉ የቃሪያ ዝርያዎች፤
  • የካሮት ዝርያ ናንተስ፣
  • የቆስጣ ዝርያ ፎርድሁክ ጂያንት፤
  • ቀይ ስር ዲትሮይድ ዳርክ ሬድ፤
  • የሰላጣ ዝርያ ግራትሌክስ ወይም ፓሪስ አይስላንድ በሚል ስሙን በመጥቀስ የተመረተበትንም ሃገር በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው።
  1. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጓሮ አትክልት ዘር፣ ዓይነት እና የዝርያ ሁኔታ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ናሙና ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የሚቀርበው ዋጋ በየዝርያው ተለይቶ የአንድ ኪሎ ግራም መሸጫ ዋጋ ሊሆን ይገባል፡፡
  3. የጓሮ አትክልቱ ዘር እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2025 የተመረተና የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜውም (Expired date) ከ2028 ያላነሰ ቢሆን ይመረጣል፡፡
  4. ተጫራቾች የጓሮ አትክልቱን ዘር የሚያቀርቡበትን የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ በስንት ቀናት ውስጥ ለድርጅቱ እንደሚያስረክቡ በዋጋ ማቅረቢያው ላይ ግልፅ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚሸጡበትን ዋጋ በማወዳደሪያ ቅፅ /ፕሮፎርማ/ ላይ በመሙላት በኤንቨሎፕ አሽገው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7ኛው ቀን በሀዋሳ ከተማ በፌዴሬሽኑ ዋና ጽ/ቤት ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ7ኛው ቀን በሀዋሳ ከተማ በፌደሬሽኑ ዋና ጽ/ቤት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ 7ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይፈፀማል፡፡
  7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- ሀዋሳ ከተማ ሞሀ የለስላሳ መጠቶች ፋብሪካ አጠገብ

ስልክ ቁጥር:- 046-2-20-98-94/82-10/09-35-97-91-46/ 09-40-28-95-86

ፋክስ ቁጥር:- 046-2-21-48-37

 

የደቡብ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ፌደሬሽን

 

Save Tender