የቦሌ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤልና ጻድቁ አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተ ክርስቲያን ከሚያከናውናቸው የልማት ሥራዎች ውስጥ አንዱ የሆነውን እና የግንባታ ሥራው በማጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ከመጪው 2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ ወደ ሥራ በማስገባት እና በማስተዳደር በትብብር ለመሥራት የሚችል ግለሰብ ወይም ተቋም ይፈልጋል።
የቦሌ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤልና ጻድቁ አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተ ክርስቲያን
ትምህርት ቤት በትብብር የማስተዳደር ጨረታ ማስታወቂያ
የቦሌ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤልና ጻድቁ አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተ ክርስቲያን ከሚያከናውናቸው የልማት ሥራዎች ውስጥ አንዱ የሆነውን እና የግንባታ ሥራው በማጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ከመጪው 2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ ወደ ሥራ በማስገባት እና በማስተዳደር በትብብር ለመሥራት የሚችል ግለሰብ ወይም ተቋም ይፈልጋል።
በዚም መሠረት በአጋርነት ለመሥራት ፍላጎት፡ ችሎታና ልምድ ያላችሁ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና በተመሳሳይ ሥራ የመልካም አፈጻጸም ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ ግለሰቦችም ሆነ ተቋማት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት አስር የሥራ ቀናት ውስጥ በደብሩ የመጠለያ ሕንጻ አንደኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው የልማት ኮሚቴ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) ከፍሎ በመውሰድ በታሸገ ፖስታ /ኢንቨሎፕ/ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለልማት ኮሚቴው ጽ/ቤት እንድታቀርቡ እንጋብዛለን።
ጨረታው የደብሩ ሰበካ ጉባኤ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ሰብከት ተወካዮች፣ የቦሌ እና ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተወካዮች፣ የልማት ኮሚቴ እና የአስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ተጫራቾቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በጨረታው ማስገቢያ የመጨረሻ ዕለት ማግስት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በሰበካ ጉባኤው አስተዳደር ጽ/ቤት ይከፈታል።
የሰበካ ጉባኤው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
የደብሩ ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር
