Tender Detail

Tender Details

  • Company New Leaf Fertility (ኒውሊፍ ሕክምና ኮምፕሌክስ)
  • Address ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፤ ለቡ አካባቢ ወይም ቫንቴጅ የጉዞና ቱር አገልግሎት፣ ብስራተ ገብርኤል፣ ሳን ሕንፃ፣ ኤም ወለል ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251984545545
  • Websitehttps://newleaffertility.org/
  • Deadline14 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-11-14 00:00:00
  • Categories Security Service

ኒውሊፍ ሕክምና ኮምፕሌክስ (በምሥረታ ላይ) ለሚቋቋመጡ ዘመናዊ የሕክምና ማዕከል ለ24 ሰዓትና ለ7 ቀን የጥበቃ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል በቂ ልምድ፣ ብቃትና ፈቃድ ያላቸውን የጥበቃ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

New Leaf Fertility (ኒውሊፍ ሕክምና ኮምፕሌክስ)


 

የግል የጥበቃ አገልግሎት አቅራቢዎች ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ የጨረታው ማጠቃለያ መረጃ

 

ዝርዝር መረጃ (Detail) ኩባንያችን ኒውሊፍ ሕክምና ኮምፕሌክስ (በምሥረታ ላይ) አድራሻ አዲስ አበባ፣ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፤ ለቡ አካባቢ የጨረታ ማስረከቢያ አድራሻ ቫንቴጅ የጉዞና ቱር አገልግሎት፣ ብስራተ ገብርኤል፣ ሳን ሕንፃ፣ ኤም ወለል የመጨረሻ ማስረከቢያ ቀን ኅዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የጨረታው ዓላማ ለህክምና ኮምፕሌክስ (Medical Complex) ዘመናዊና አስተማማኝ የጥበቃ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም መቅጠር።

የጨረታ መመሪያና የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

ኒውሊፍ ሕክምና ኮምፕሌክስ (በምሥረታ ላይ) ለሚቋቋመጡ ዘመናዊ የሕክምና ማዕከል ለ24 ሰዓትና ለ7 ቀን የጥበቃ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል በቂ ልምድ፣ ብቃትና ፈቃድ ያላቸውን የጥበቃ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

  1. የአገልግሎት ዓይነት

የጥበቃ ተቋሙ የሚጠበቅበት አገልግሎት የሚከተሉትን ዋና ዋና ጉዳዮች ያጠቃልላል-

  • የ24/7 አካላዊ ጥበቃ: በሁሉም የመግቢያ፤ መውጫና ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ላይ በቂ እና የስለጠኑ ሰራተኞችን ማሰማራት፡፡
  • የሕክምና ተቋም ተሞክሮ: የሕክምና ማዕከልን ተፈጥሮ (ለታካሚዎች እና ጎብኚዎች ያለውን ስሱነት) የሚረዳና በብቃት የሚያስተዳድር የጥበቃ ኃይል ማሰማራት፡፡
  • የንብረት ደህንነት: የህንፃዎችን፣ የመሳሪያዎችን (በተለይም የላቁ የሕክምና ቴክኖሎጂዎችን) እና የፓርኪንግ ቦታዎችን ደህንነት ማስጠበቅ።
  • የክትትል ስርዓት አጠቃቀም: በኮምፕሌክሱ ውስጥ የተገጠሙ የደህንነት ካሜራዎችንና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ የክትትል ስርዓቶችን በብቃት መጠቀም/መቆጣጠር።
  1. የሰራተኞች የስራ ሰዓት ዝግጅት

የጥበቃ ሰራተኞች የፈረቃ ዝግጅት መቅረብ አለበት፡፡ ይህ ዝግጅት ኮምፕሌክሱ የሚፈልገውን የ24 ሰዓት ቀጣይነት ያለው ሽፋን ማረጋገጥ አለበት።

  • ተጫራቾች የሰራተኞቻቸውን የዕለት ተዕለት የፈረቃ ዝግጅት (Shift Schedule) በጽሑፍ ማቅረብ አለባቸው።
  • የጥበቃ ሰራተኞች በፈረቃ መካከል በቂ እረፍት እንዲያገኙና በተቋሙ ውስጥ የጥበቃ ክፍተት እንዳይፈጠር የሚያረጋግጥ ዕቅድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  1. ዋጋ

የዋጋ ዝርዝር (Price Quotation) ግልጽና ዝርዝር ሆኖ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

  • የሚቀርብ መረጃ: ለጥበቃ አገልግሎት የሚያስፈልገው አጠቃላይ ወርሃዊ የዋጋ ግምት፡፡
  • የወጪ ዝርዝር: ዋጋው የጥበቃ ሰራተኛ ደመወዝ፣ የደንብ ልብስ፣ የክትትል ወጪ፣ የሱፐር ቫይዘር ወጪ እና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎችን በዝርዝር አካቶ መቅረብ አለበት፡፡
  • የግብር ሁኔታ: ዋጋው ከቫት (VAT) በፊት እና ከሻት በኋላ ተብሎ በግልጽ መለያየ አለበት፡፡
  1. የአፈጻጸም ማረጋገጫ

ተጫራቾች አገልግሎት ለመስጠት ያላቸውን ብቃትና ልምድ ማረጋገጥ አለባቸው፡፡

  • ተፈላጊ ማረጋገጫ: በተለይም ከሕክምና ተቋማት ወይም ከሆስፒታሎች ጋር ተያያዥ ያላቸውን የተጠናቀቁ ወይም በአሁኑ ጊዜ እየሰጡ ያሉ አገልግሎቶችን ማቅረብ።
  • የድጋፍ ደብዳቤ: ቢያንስ ሁለት (2) ከአሁን በፊት አገልግሎት ከሰጡዋቸው ድርጅቶች (በተለይ ከሆስፒታሎች) የተሰጡ የምስክርነት ወይም የድጋፍ ደብዳቤዎችን (Refere Letters) ማቅረብ።
  1. ሌሎች

በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የሚከተሉት ተጨማሪ መረጃዎች መካተት አለባቸው።

  • የሕጋዊነት ማረጋገጫ
  • የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ።
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ኮፒ፡
  • የቫት/ቲኦቲ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ኮፒ፡፡
  • ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወይም ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የጥበቃ አገልግሎት ፈቃድ
  • የድርጅቱ አቅም:
  • የድርጅቱ መዋቅር እና ቁልፍ አመራሮች የት/ት እና ስራ ልምድ ማስረጃ።
  • የጥበቃ ሰራተኞች የስልጠና ዝርዝር እና ቅጥር መመዘኛ።
  1. የጨረታ ማስረከቢያ ሁኔታ
  • ተጫራቾች ሁሉንም ስነዶች በአንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ በማድረግ፣ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  • ኤንቨሎፑ የድርጅቱን ስም፤ አድራሻ እና “የጥበቃ አገልግሎት ጨረታ ሰነድ” የሚል ጽሑፍ በግልጽ መያዝ አለበት፡፡
  • የዋጋ ዝርዝር እና ቴክኒካዊ ሰነዶች (ቴክኒካል ፕሮፖዛል) ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ ሆነው በአንድ ትልቅ ኤንቨሎፕ ውስጥ መግባት አለባቸው።
  • በኅዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 11 ሰዓት በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251984545545 መጠየቅ ይችላሉ።

 

 

Save Tender