ራስ አገዝ የሴቶች ድርጅት (ራሴድ) በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በአሚኛ ወረዳ -ባሞ ቀበሌ፣ በጢቾ ወረዳ - ኮረብታ ቀበሌ እና በሮቤ ወረዳ-አቧሊ ቀበሌ ከHumundi ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ አማካኝነት እየተገበረ ለሚገኘው ፕሮጀክቱ የኮንስትራክሽን ተጫራቾችን በመጋበዝ የገ/ቁ/ብ/ህ/ስ/ማህበራትን ቢሮ ማሰራት ይፈልጋል።
Organization for Women in Self Employment (WISE) (ራስ አገዝ ሴቶች ድርጅት (ራሴድ))
ራስ አገዝ ሴቶች ድርጅት (ራሴድ)
የኮንስትራክሽን ስራ ጨረታ ማስታወቂያ
ራስ አገዝ የሴቶች ድርጅት (ራሴድ) በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በአሚኛ ወረዳ -ባሞ ቀበሌ፣ በጢቾ ወረዳ - ኮረብታ ቀበሌ እና በሮቤ ወረዳ-አቧሊ ቀበሌ ከHumundi ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ አማካኝነት እየተገበረ ለሚገኘው ፕሮጀክቱ የኮንስትራክሽን ተጫራቾችን በመጋበዝ የገ/ቁ/ብ/ህ/ስ/ማህበራትን ቢሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ደረጃ 6 እና ከዛ በላይ የሆናችሁ ተጫራቾች የንግድና ምዝገባ ፍቃድ፣ የቫት፣ ቲን እና የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፤ የብቃት ማረጋገጫ ፣የታክስ ክሪላንስ ሰርተፍኬት 6ወር ያላለፈው እንዲሁም የስራ ልምዳችሁን የሁሉንም ዋናውን እና ኮፒ ማቅረብ ይገባችኋል።
ለዚህም የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ንፋስ ስልክ ማሞ ኮንዶሚኒየም አጠገብ ከሚገኘው ቢሯችን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። ጨርታው አርብ ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም 9፡00 ላይ ተዘግቶ በእለቱ 9፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻችው በተገኙበት ይከፈታል። ድርጅቱ የተሻል አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ከዚህ በታች ባለው ስልክ ቁጥር መደወል የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ስልክ ቁጥር 0911880061
ራስ አገዝ ሴቶች ድርጅት (ራሴድ)
