Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
  • Address ሀዋሳ ከተማ አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-212-13-34
  • Website
  • Deadline24 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price700.00
  • Bid Security100,000.00
  • opening date2025-11-24 00:00:00
  • Categories Construction Works

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሆዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራከሸን መምሪያ በሁሉም ክ/ከተሞች ለሚያስራጡ ነባሪ የጎርፍ መውረጃ ቦይ ጥገና እና ኮብልስቶን መንገድ ጥገና ሥራ አስር(10) ሎቶችን በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ያስፈለገ በመሆኑ በተዘጋጀው ዲዛይን ተጠቅሞ በዘርፉ ፈቃድ ካለው በጥቃቅንና አነስተኛ ደረጃ የተደራጁ ማህበራት መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ


ጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሆዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራከሸን መምሪያ በሁሉም ክ/ከተሞች ለሚያስራጡ ነባሪ የጎርፍ መውረጃ ቦይ ጥገና እና ኮብልስቶን መንገድ ጥገና ሥራ አስር(10) ሎቶችን በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ያስፈለገ በመሆኑ በተዘጋጀው ዲዛይን ተጠቅሞ በዘርፉ ፈቃድ ካለው በጥቃቅንና አነስተኛ ደረጃ የተደራጁ ማህበራት መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት

1. በኮንስትራከሽን ዘርፍ በጥቃቅንና አነስተኛ ደረጃ የተደራጁ ማህበራት፡-

2 በሥራ መስኩ ሀጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብርመክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ!

4. የእቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣ በጨረታው እንዲሳተፍ የታከስ ከሊራንስ ማቅረብ አለበት፣ የብታት ማረጋገጫ ምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡-

5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 /ለሃያ/ ተከታታይቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 700 (ሰባት መቶ ብር) በመከፈል ወስዶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር፤ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንከ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ ፒ አ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት ፡፡

7. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ (ቴከኒካል እና ፋይናንሻል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 20(ሃያ) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግገር ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8. ጨረታው በ21ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት፤ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች በሲዳማ ክልል እና ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ተመሳሳይ ሥራ በእጁ ላይ ካለና የሥራው አፈጻጸም 70% ካልደረሰ በጨረታ መወዳደር አይችልም፡፡ ሥራው 70% እና በላይ የደረስ ከሆነ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማረጋጋጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

 

10. በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲክ ቼከ በሚደረግበት ጊዜ በሁለቱ መካከል ከ5% (ከሁለት ፐርሰንት) በላይ ሆነ በታች ልዩነት ካለ ተጫራቹ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡

11. ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ላይ ከአሥራ አምስት ፐርሰንት (15%) በላይከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡

12. ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ታች ከሃያ እስከ ሰላሳ ፐርሰንት (20% እስከ 30%) በታች ከሆነ በተሰበረው ተብለው ተይዞ የሚያልፍ ይሆናል፡፡

13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡

 ስልክ ቁጥር 046-212-13-34

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና/ኢኮ/ል/መምሪያ ሀዋሳ

Save Tender