Tender Detail

Tender Details

  • Company በደ/ኢ/ከ/መንግሥት በጎፋ ዞን ጋልማ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address በጎፋ ዞን ጋልማ ከተማ ፣ በደ/ኢ/ክ/መንግሥት ፣ ኢትዮጲያ, Phone: 0936481270
  • Website
  • Deadline17 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price600.00
  • Bid Security200,000.00
  • opening date2025-11-17 00:00:00
  • Categories Construction Works

በደ/ኢ/ከ/መንግሥት በጎፋ ዞን ጋልማ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለጋልማ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ግንባታ በ2018ዓ.ም በተያዘ በጀት ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በደ/ኢ/ከ/መንግሥት በጎፋ ዞን ጋልማ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


የግንባታ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር- ጋከ/አስ/ፋ/ግ/ን/አስ/ር/ግ/ጨማ/18

በደ/ኢ/ከ/መንግሥት በጎፋ ዞን ጋልማ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለጋልማ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ግንባታ በ2018ዓ.ም በተያዘ በጀት ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  • የጨረታ ዓይነት:- ግልጽ ጨረታ
  • የዘመኑን ግብር የከፈሉና ያሳደሱ፣በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN No. ያላቸው፣
  • የተጫራች ደረጃ ስምንት እና ከዚያ በላይ፣የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው፣
  • በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመካተታቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  • መልካም የሥራ አፈፃፀም ምስከር ወረቀት ከ2016 ዓ.ም ወዲህ ማቅረብ የሚችል፣
  • ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልጾላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  • የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ብር በባንክ በተረጋገጠ cpo ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • የጨረታውን ሰነድ ከጋልማ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ሥራ ከፍል ቀርበው የማይመለስ ብር 600/ስድስት መቶ/ በመከፈል ሰነድ መግዛት የሚችሉ፣
  • ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ በመሙላት ቴከኒካል አንድ ኦሪጅናል ከ2 ኮፒ ጋር እና ፋይናንሻል አንድ አሪጂናል ከ2 ኮፒዎች ጋር በተናጠል በእናት ፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከቀን 20/2/2018ዓ.ም ጀምሮ ጨረታው ለ16 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ17ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ላይታሽጎ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ባይገኙም የጨረታውን መከፈት አያስተጓጎልም፡፡
  • ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘረዘረው መጠይቅ መሠረት ብቻ ዋጋውን ሞልቶ በመፈረምና ሕጋዊ የድርጅቱን ማህተም በሁሉም ገጽ ማሳረፍ አለባቸው፡፡
  • አሸናፊው ድርጅት ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ከአሠሪው መ/ቤት ጋር ውል መግባት አለበት፡፡
  • ጨረታው የሚታሸግበት ቀን ቅዳሜ፣እሁድ ወይም ከሥራ ቀን ውጪ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀንና በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0936481270/ 0942071683 / 0916725503

በደ/ኢ/ክ/መንግሥት በጎፋ ዞን ጋልማ ከተማ አስተዳደርፋ ይናንስ ጽ/ቤት

ለጋልማ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት

Save Tender