በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የእንቁላል ዶሮና ኬጅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የእንቁላል ዶሮና ኬጅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1. ተጫራቶች በመንግስት ግዥ በዕቃ አቅራቢነት ውስጥ የተመዘገቡ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች እኛ ከሰጠነው የጨረታ ሰነድ የዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ውጪ ሞልቶ የሚያቀርብ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
3. ተጫራቾች ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
5. ገዥው መ/ቤት ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከተዋዋለበት ቀን ጀምሮ በጀት ዓመቱ እስኪጠናቀቅ ትዕዛዝ ይችላል፡፡
6. ተጫራቾች በተሰጣቸው በዶሮ እርባታ ዘርፍ ብቻ መሳተፍ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች የመስሪያ ቦታቸውን ከጨረታ መክፈቻው በፊት ማስጎብኘት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
9. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በቂ/ክ/ከ/የወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት ውስጥ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
11. ተጫራቾች ለጨረታው ያቀረቡትን ዋጋ የሚቆይበትን ጊዜ ቢያንስ ለ 60 ቀን መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
12. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቂ/ከ/ከ/የወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡
13. የወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 011-515-88-38
አድራሻ፡ ብሄራዊ ከበድሉ ህንጻ በስተጀርባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት
