Tender Detail

Tender Details

  • Company Central Ethiopia regional state justice Bureau (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፍትህ ቢሮ)
  • Address ሀላባ ቁሊቶ ከተማ : ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046556250-
  • Websitehttps://www.cerjustice.gov.et/
  • Deadline09 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-11-09 00:00:00
  • Categories Office Machines And Computers , Office Machines And Accessories , Office Equipment

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የፍትህ ቢሮ አገልግሎት የጽ/መሳሪያዎችንና የቢሮ አላቂ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Central Ethiopia regional state justice Bureau (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፍትህ ቢሮ)


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የፍትህ ቢሮ አገልግሎት የጽ/መሳሪያዎችንና የቢሮ አላቂ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin no) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችለ፣
  3. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የፍትህ ቢሮ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ድርጅቶች የተጨማሪ እሴት ታክስን በማካተት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) በማሸግ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ተከታታይ የስራ ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የፍትህ ቢሮ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 በመቅረብ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታው ሳጥን በዚሁ ዕለት ማለትም /በ10ኛው ቀን/ ከሰዓት 11፡30 ሰዓት ላይ ይታሸግና በ11ኛው ቀን ጠዋት በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰአት ይከፈታል።
  7. አሸናፊዎች ማሸነፋቸው ከተረጋገጠ በኋላ የተወዳደሩበትን የዕቃ አይነት ናሙና/Sample ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046 556 250 በስራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በማዕ/ኢት/ክልላዊ መን/የፍትህ ቢሮ ግዢ፣  ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት /ሀላባ ቁሊቶ

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፍትህ ቢሮ

Save Tender