የግቤ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት አገልግሎት ያቆመውን 1/ አንድ/ አሮጌ መኪና እና 17 ሱዝክ የተለያዩ ሞተር ሳይክል በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በሀዲያ ዞን የግቤ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ሰነድ ቁጥር-001
የግቤ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት አገልግሎት ያቆመውን 1/ አንድ/ አሮጌ መኪና እና 17 ሱዝክ የተለያዩ ሞተር ሳይክል በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ሽያጭ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ሁሉ፡-
1. ተጫራቾች ህጋዊ የሆነ ንግድ ፈቃድ/ የታደሰ መታወቂያ እና ሌላም በዘርፉ መረጃ ማያያዝ ይኖርበታል፡-
2. የመኪና እና የሞተር ሳይከል ባሉበት ሁኔታ አባሪ በተደረገው ሠንጠረዥ ላይ ተመልከቷል፡፡
3. የመወዳደሪያ ሀሳቡ /የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ ሆኖ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀናት ውስጥ እስከ 4:30 ሰዓት ለግዥ ፈጻሚ መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 18 መድረስ አለበት፡፡
4. የመወዳደሪያ ሀሳቡ የሚከፈተው አቅራቢዎች/ሕጋዊ ወኪሎች/ በተገኙበት በı5ኛ ቀን 5፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡ የአቅራቢዎች/ሕጋዊ ወኪሎች/ አለመገኘት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ /የመወዳደሪያ ሀሳብ/ የመከፈት ሂደትን እያስተጓጉልም።
5. የመኪና መረከቢያ ቦታ ግቤ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ሆኖ የመኪና/ሞተር ሐራጅ ሽያጭ ጨረታ ካሸነፈበት ጊዜው ሽያጭ ካዘዘበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ይሆናል።
6. አቅራቢዎች ጠቅላላ ዋጋውን በቁጥርና በፊደል መጻፍ አለባቸው፡፡ በቁጥርና በፊደል በተገለጸው የዋጋ መጠን መካከል አለመጣጣም ካለ በፊደል የተገለጸው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ በነጠላ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5% ብር 60,000/ ስልሳ ሺህ ብር ብቻ/በግቤ ወረዳ ፋይናንስ ስም በ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ /በሁኔታዎች ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወረቀት/ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ የጨረታ መነሻ ዋጋ የመኪና 1,200,000/አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ሲሆን ለሞተሮች ባሉበት ሁኔታ ለ17 ሞቶሮች 18,000/አስራ ስምንት ሺህ ብር ብቻ ነው።
8. ተጫራቾች የሚሸጠውን መኪና እና ሞተር ሳይክል ለማየት ከፈለጉ ጨረታው እስከሚዘጋበት ጊዜ ውስጥ በግቤ ወረዳ ፋይናንስ በአካል በመገኘት ማየት ይችላሉ።
9. የጨረታው አሸናፊ መሸነፉን በፅሁፍ ከተገለጸበት ከ6ኛ ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈጸም የጨረታ አሸናፊነቱ ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ የጨረታ አሸናፊ ከመ/ቤቱ ጋርውል ከተፈራረመበት ጊዜ አንስቶ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ጠቅላላ በመከፈል የትራንስፖርትና መጫኛ ወጪ ችሎ ከግቢ ማንሳት አለበት። ይህ ባይፈፀም በውሉ በተቀመጡ ግዴታዎች መሠረት አሸናፊው ድርጅት ተጠያቂ ይሆናል።
10. ጨረታው የውል ማስከበሪያ ለተሸናፊዎች የጨረታ አሸናፊው ውል ከተፈራረመበት ጊዜ አንስቶ ዘወትር በሥራ ሰዓት ተመላሽ ይሆናል፡፡
11. የመወዳደሪያ ሀሳብ /የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ/ ማቅረቢያ ቋንቋው በአማርኛ ነው፡፡
12. መኪና እና ሞተር ሳይክል መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች/specification/ተያይዟል፡፡
13. አሸናፊው የሚለየው የመኪና እና ሞተር ላይ ብቻ መቅረብ የሚችል ሲሆን/ያቀረበው/ በጠቅላላ ዋጋ/ ሎት በሎት/ ከፍተኛ ዋጋ በዚህ መስፈርት መሠረት ለሁሉም የመኪና እና የሞተር ዋጋ ላይብቻ ተጫራቾች ዋጋ መቅረብ ይችላሉ፡፡
14. ማንኛውም ተጫራች ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት የዋጋ ማቅረቢያ ሠነዱን/ የመወዳደሪያ ሀሳብ/ማስገባት ይኖርበታል፡፡
15. ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የቀረበ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ /የመወዳደሪያ ሀሳብ/ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ኤንቨሎፑ ሳይከፈት ለተጫራች ተመላሽ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
16. የመወዳደሪያ ሀሳቡ የሚቀርበው በኢትዮጵያ ብር ይሆናል፡፡
17. ከጨረታ ሠነድ ማስረከቢያ ሰዓት በፊት የቀረቡ የጨረታ ኤንቨሎፖች በሙሉ ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በኋላ ወዲያውኑ ይከፈታሉ።
18. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500/አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግቤ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡
20. የጨረታ መወዳደሪያው በሚከተለው መሠረት ይሆናል፡፡ በቀረበው ዋጋ ላይ የሂሳብ ድምርስህተት ካለ እንዲታረም ይደረጋል፡፡ ውድድሩ የሚካሄደው እና ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢው የሚለየው በታረመው ዋጋ መሠረት ይሆናል፡፡ ያቀረቡት ዋጋ በቁጥርና በፊደል መግለጽ አለበት፡፡
21. ጨረታው የቴከኒክ መስፈርቱን ካሟሉት አቅራቢዎች መካከል ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች አሸናፊ ይደረጋል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኛ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ 0462510006 ወይም ሞባይል ቁጥር 0913906521
በሀዲያ ዞን የግቤ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
