Tender Detail

Tender Details


የሸኖ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በኦሮሚያ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሙያ ቢሮ ለሸኖ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ለተለያዩ መ/ቤቶች የተለያዩ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል የሸኖ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ፡-ግ/ጨ/ቁ 02/2018

 

የሸኖ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በኦሮሚያ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሙያ ቢሮ ለሸኖ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ለተለያዩ መ/ቤቶች የተለያዩ፡

  • Building construction material
  • ICT & Electronics Material
  • Automotive material
  • Metal and welding material
  • Electrical electronics
  • Material for BEI

የተለያዩ የህትመት ዉጤቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በየሥራ ዘርፉ የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፤ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላችሁ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ "VAT 15%" ተመዝጋቢ የሆናችሁ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያላችሁ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሸኖ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ዝርዝር መጠይቆችን የያዘውን ሰነድ በማይመለስ በብር 800 በካሽ መግዛት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በዝርዝር የተመለከተውን የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና በካሽ ወይም ሲፒኦ CPO ማስያዝ አለባቸው።

ተጫራቾች በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ በ16ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ውሉን ፈጽሞ እቃዎችን የማስገባት ግዴታ አለበት፡፡

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ (አማራጭ) ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ፡- ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ 78 ኪሎ ሜትር ሸኖ ከተማ ነው::

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0910 093362 በመደወል ጠይቆ መረዳት ይቻላል፡፡

 

በኦሮሚያ ክልል የሸኖ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender