Tender Detail

Tender Details

  • Company በደ/ኢ/ክ/መንግስት በኮንሶ ዞን የካራት መ/ደ/ሆስፒታል
  • Address ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-02-92-81-00
  • Website
  • Deadline19 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Security50,000.00
  • opening date2025-11-19 00:00:00
  • Categories Construction Works

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በኮንሶ ዞን የካራት መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት የሠራተኞች መመገቢያ ህንፃና የአስከሬን ከፍል ግንባታ በመንግሥት የግዥ መመሪያ መሠረት በግንባታ ዘርፍ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በደ/ኢ/ክ/መንግስት በኮንሶ ዞን የካራት መ/ደ/ሆስፒታል


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በኮንሶ ዞን የካራት መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት የሠራተኞች መመገቢያ ህንፃና የአስከሬን ከፍል ግንባታ በመንግሥት የግዥ መመሪያ መሠረት በግንባታ ዘርፍ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

1. በዘርፉ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤

2. የአቅራቢነት ንግድ ምዝገባ ምስከር ወርቀት ያላቸው፤

3. ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ያላቸው፣

4. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር TIN No ያለው

5. የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የምስከር ወረቀት ያለው፤

6. የብቃት ማረጋገጫ GC& BC-7 ከዚያም በላይ የሆነ፤

7. የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነድ 50,000/ሃምሳ ሺህ/ ብር ብቻ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO በቴክኒካል ኦርጂናል ፖስታ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይቻላል፡፡

8. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21/ሃያ አንድ ቀናት/ ቅዳሜና ዕሁድን እና የበዓላት ቀናትን ጨምሮ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 400 /አራት መቶ ብር/ ብቻ ክፍያ ሂሳብ ክፍል በመክፍል የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀ ሰነድ መውሰድ ይቻላል።

9. ተጫራቾች ቴከኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ ተሞልቶ አንድ ኦርጂናልና እና ሁለት ኮፒ በተለያየ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡

10. ተጫራቾች በሁለቱም ፖስታዎች ላይ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ስም ፊርማና አድራሻ በማሳረፍ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማድረግና በትክከል በማሸግ 22ኛው የሥራ ቀን 4፡00 - 4፡30 ሰዓት ላይ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል በመገኘት ለጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

11. የጨረታ ሳጥን የሚከፈተው በዚሁ ዕለት በ 4፡31 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከረፋዱ 4፡ 40 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ

ጨረታው የሚከፈትበት 22ኛው ቀን የመንግሥት መደበኛ የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡

 

በጨረታው መከፍቻ ዕለት ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ አለመሟላት የጨረታ አከፋፈት ሂደት አያስተጓጉልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሚሆን ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልፆ በሚሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ተገቢውን መፈፀም አለበት። አሸናፊው ከተለየ በኋላ ራሱን ከጨረታ የሚያገለግል ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ለመ/ቤቱ ውርስ ሆኖ አግባብ ባለው ህግ ይጠይቃል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ስልክ ቁጥር 09-02-92-8100/0984695237/ ደውለው መጠየቅ

በደ/ኢ/ክ/መንግሥት በኮንሶ ዞን የካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

Save Tender