በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን የደጎሎ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለደጎሎ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ሎት 2 ኤሌክትሮኒከስ፣ሎት 3 ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የደጎሎ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን የደጎሎ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለደጎሎ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ሎት 2 ኤሌክትሮኒከስ፣ሎት 3 ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፤
4. የግዥ መጠን ከብር 200,000 ብር (ሁለት መቶ ሺህ ብር ) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ በቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤
5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፤
6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስማቸውን፤ፈርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማሳረፍ ይጠበቅባቸዋል፣
7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ ከጨረታው ውድቅ የሚያደርግ መሆኑን አውቀው በጥንቃቄ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፤
8. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የስራ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ ፤
9. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ለመግዛት ለእያንዳንዳቸው ሎቶች የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ/ብርበመክፈል በመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 1 መግዛት ይችላሉ፥
10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ በመ/ሂ 1 ማስያዝ ያለባቸውና የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተፃፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በመ/ቤቱ እስፔስፊኬሽን መሠረት ለአሸነፉባቸው ለእያንዳንዱ እቃዎች ናሙና በማቅረብ ውል መውሰድ አለባቸው፤
11.ማንኛውም ተጫራች ሀሳቡን በእንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ኦርጅናል ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በደጎሎ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት በግ/ፍ/ን/አስ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
12. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ይዘጋል፡፡ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታ ሆኖም ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን እና ካሉት የስራ ቀናት ውጪ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፤
13. መ/ቤቱ በጨረታው የሚገዙ እቃዎች ላይ 20% የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
14. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፤
15. ማንኛውም ተጫራች ግዥው በጥቅል (በሎት) የሚፈፀም መሆኑን አውቆ ለእያንዳንዳቸው ዝርዝርዕቃዎች ዋጋ መሙላት ይኖርበታል፡፡ የተዘረዘሩትን እቃዎች በሙሉ ለእያንዳንዳቸው እቃ ያለመሙላት ከጨረታው ውድቅ የሚያስደርግ ሲሆን አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ገቢ አድርገው ሳያጠናቅቁ ክፍያ የማይፈፀም መሆኑን እና በውለታው መሠረት ዕቃውን ጨርሰው ለመ/ቤቱ የማስረከብ ግዴታ አለባቸው፤
16. እያንዳንዱ ተጫራች ጨረታውን መሙላት ያለበት ከታከስ ጋር ነው፡፡ ከታክስ ጋር ያለመሙላት ከጨረታው ወድቅ ያስደርጋል፤
17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
18. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለ ጨረታው መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0902691555 /09202031235 ላይ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የደጎሎ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
