Tender Detail

Tender Details


የባቱ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት አመት በስሩ ለሚተዳደሩ ባለበጀት መ/ቤቶች የተለያዩ 1ኛ- የኢንዱስትሪ የግንባታ ዕቃዎች (Industry Materials)፣ 2ኛ- ሎካል የግንባታ ዕቃዎች (Local Construction Materials) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የባቱ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


 

የግንባታ ዕቃ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የባቱ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት አመት በስሩ ለሚተዳደሩ ባለበጀት መ/ቤቶች የተለያዩ 1ኛ- የኢንዱስትሪ የግንባታ ዕቃዎች (Industry Materials)፣ 2ኛ- ሎካል የግንባታ ዕቃዎች (Local Construction Materials) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ በመሙላት፤ ያሸነፉበትን ዕቃ እስከ ባቱ/ዝዋይ ከተማ ገንዘብ አሰተዳደር ጽ/ቤት ድረስ የሚያቀርቡበትን የመጓጓዣ የማስጫኛ እና ማውረጃ ወጪውን በመጨመር ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

1ኛ- ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣

2ኛ- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በሚጫረቱበት ዘርፍ የተመዘገቡ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3ኛ- ተጫራቾች የንግድ ሥራ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ ስለመሆናቸው ማስረጃ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) እና የቫት (VAT) ሰርትፍኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

4ኛ- የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30- 11፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፣

5ኛ- ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ 1000 (አንድ ሺህ ብር ብቻ) ለአንዱ ሰነድ በመክፈል ከመ/ቤታችን የግዥና ንብረት አስተደደር የሥራ ሂደት ክፍል መግዛት ይችላሉ፤

6ኛ- ተጫራቾች ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ለአንዱ ሰነድ ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) በባቱ/ዝዋይ ከተማ ገ/አስተዳደር ጽ/ቤት ስም አስገብቶ ከጨረታ ሰነድ ፋይናንሻል ኦርጅናል ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7ኛ- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ የዋጋ ሰነድ በጥራት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመስሪያ ቤቱ ጥያቄ መሰረት ብቻ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻውንና የተወዳደሩትን ዕቃ አይነት 18/02/2018 ዓ.ም እስከ 09/03/2018 ዓ.ም 8:00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8ኛ- ጨረታው በ09/03/2018 ዓ.ም 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም በባቱ ከተማ ገ/አስተዳደር ጽ/ቤት የግዥና ንብራት አስተዳደር የሥራ ሂደት ክፍል ይከፈታል፡፡

9ኛ- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ/መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-45-38-94-44/0911-51-02-44/ ደውለው ይጠይቁ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በበዓልና በዝግ ቀናት ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን ላይ ይሆናል፡፡

 

የባቱ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender