በአብክመ በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃላ/የተ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሎት 1 - ኤሌክትሮኒከስ (ላፕቶፕና ሞባይል ቀፎ እና ሎት 2 -የሞተር ብስክሌት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው መግዛት ይፈለጋል፡፡
መርከብ ሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒየን ኃላ/የተወሰነ
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃላ/የተ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሎት 1 - ኤሌክትሮኒከስ (ላፕቶፕና ሞባይል ቀፎ እና ሎት 2 -የሞተር ብስክሌት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው መግዛት ይፈለጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin No/ ያላቸው መሆን አለባቸው::
2. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንከ ጋራንቲ /ዋስትና⁄ ወይም ሲፒኦ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
3. የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነበት የተጨማሪ እሴት ታከስ /ቫት/ እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆነ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታከስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዘ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና 1 (CPO) ሲያስይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው አንዱ ወይም በጥቅል ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
4. ማንኛውም ተጫራች ሰነዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ከብ ማህተም በማድረግ አና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታ ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ 1-ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
6. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 350 ብር በመክፈል 1-የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለioi ተከታታይ የስራ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ከፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 101 መግዛት ይቻላል፡፡
7. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን ተከታታይ ቀናት ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት በ8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
8. ቅዳሜ የዩኒየኑ የስራ ቀን ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
9. የጨረታው ተወዳዳሪዎች /ተወካዮቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆንየተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
10. የጨረታው አሸናፊ በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ በማስያዝ ውል መፈጸም አለባቸው፡፡
11. ከአንድ ሎት ውስጥ ቀንሶ (መርጦ) መሙላት አይቻልም አሸናፊው የሚለየው በተናጠል ይሆናል፡፡አሸናፊው ያሸነፈውን በፍትህ ውል ከተመርመረ (ከተመዘገበ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ከፍያ አሸናፊው ይከፍላል/ይሸፍናል፡፡
12. የሚገዛን ንብረት (እቃ) ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ማንኛውንም የወዛደር ማስጫኛ አና የትራንስፖርት ወጪ በአሸናፊው የሚሸፍን ይሆናል፡፡ የሚገዛ እቃ ብዛት አና መለያ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኝ ይገኛል፡፡
13. በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማ የግዢና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
14. የኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር፡- 09-11-59-05-34/ 09-10-63-46-46 መጠየቅ ይቻላል፡፡
መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ//ማ/ዩኒየን ኃላ/የተ
