በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ለመምሪያውና በስሩ ለሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች ለስራ አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑ ተጫራቾች ከስር በየሎቱ የተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ የብርመጠን በሲፒኦ በመ/ቤቱ ስም በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ለመምሪያውና በስሩ ለሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች ለስራ አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑ ተጫራቾች ከስር በየሎቱ የተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ የብርመጠን በሲፒኦ በመ/ቤቱ ስም በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ፡፡
ሎት 1 የፅህፈት ዕቃዎች-------------የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 6,000.00
ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች ------------የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 4,000.00
ሎት 3 ኤሌክትሪክ እቃዎች--------የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 5,000.00
ሎት 4 ግንባታ እቃዎች-----------የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 5,000.00
ሎት 5 ህንፃ መሣሪያ ------------የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 6,000.00
ሎት 6 ቋሚ እቃዎች------------የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 6,000.00
ሎት 7 አልባሳት ---------------የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 5,000.00
ሎት 8 የህትመት ውጤቶች ----- የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 6,000.00
ሎት 9 ህከምና መድሀኒት ሪኤጀንትና የህከምና እቃዎች----------የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 5,000.00
ሎት 10 የኤሌከትሮኒከስ (የቢሮ መሣሪያዎች) ጥገና እና እድሣ-------የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 4,000.00
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና በጨረታው ለመወዳደር ፍላጐት ያላቸው የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ ገጽ ላይ በአቅራቢነት ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክርወረቀት ማቅረብ የሚችል እና ከግብር ነፃ መሆኑን የሚያስረዳ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ለተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 100 ብር በመከፈል የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ ልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ከቀኑ 7፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ 5ተኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 11 የስራ ቀናት በልደታ ከፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 5ኛ ፎቅ ግዥ ከፍል በተዘጋጀውሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ውጭ ዘማይዳ 98.12 ተጫራች ተቀባይነት የለውም፡፡
5. ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት መምሪያው በሚያዘጋጀው ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታው አይስተገገልም የመከፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን እሽጉ ይከፈተል።
6. ተጫራቾች እንደ አስፈላጊነቱ ናሙና/ሳምፕል/ የሚያስፈልጋቸውን እቃዎች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎቶች ናሙና ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም እንዳንድ ዕቃዎች ዝርዝር የዕቃ መለያ ፕሮፖዛል ወይም (እስፔስፊኬሽን) እና ሥሪቱ ሀገር መጥቀስ አለባቸው::
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ውጭና ከሻት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፋባቸዉን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡መስሪያ ቤቱ ተጫራቾች ከአሸነፉት እቃ ላይ 2005 የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
9. በአቅርቦትና በአገልግሎት አሠጣጥ ብቃትና ጥራት እንዲሁም በወቅቱ ማቅረባቸውን ከአሁን በፊት የተመሠከረለት ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ቢሆን ይመረጣል፡፡
10. በጉዞ ወቅት ወይም በርክከብ ወቅት የተበላሹና የተሰበሩ እንዲሁም የማይሰሩ እቃዎች ቢገኙ ወይም ተመሳስለው የተሰሩ እቃዎች ቢያስረከብ ተመላሽ የማድረግና በራሱ ወጪ የመተካት ግዴታ አለበት ለሠጠውም እቃዎች ዋስትና መስጠት ግዴታ አለበት፡፡
11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት መድሃኒት የአገልግሎት ቆይታ ጊዜ ሁለት ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ መሆን አለበት፡፡
12. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ሲያስገቡ ግዥ ክፍል ባዘገጀው ፎርም ላይ ዋጋቸውን ማስገባት አለባቸው፡፡ በራሳቸው ፎርም ዋጋቸውን ካስገቡ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፦
አድራሻ ልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጎማ ቁጠባ 5ተኛ ፎቅ ግዥ አስተዳደር ክፍል ስልክ ቁጥር0115-57-33-14 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
