የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል ሲሚንቶ ከነትራንስፖርቱ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- 06/2018
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል ሲሚንቶ ከነትራንስፖርቱ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆንም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤
3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ /NAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የሚገዛወ ሲሚንቶ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመ/ቤቱ አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 በመከፈል የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ቀን 22/2/2018 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ከፋይናንሻል ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስያዝ አለባቸው፡፡ ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 500,000.00 /ከአምስት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ብቻ ማስገባት ይችላሉ፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች የማጫረቻ ሰነድ ዋናና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በአንድ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ከ13/2/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 28/2/2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትና ሌሎች ታከስ እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት በቀን 28/2/2018 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን በ8፡30 ሰዓት ግዥ ኢፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል፡፡
11. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
12. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
13. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ አፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058-2-22-11-00 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-3-22-05-155/058-2-22-11-07 በመደወል ወይም በኤጀንሲው ድረ-ገጽ www.arrca.gov.et ማግኘት ይችላሉ፡፡
14. ተጫራቶች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርስ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠርመንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
