በጅማ ዞን በሊሙ ስቃ ወረዳ መንገድና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት የገጠር መንገድ ላንጦ አለለወርቅ፣ ሞቴ አልጋ ቂልጡ ሙጃ፣ ኮማ ጨሪ አልጋ፣ ሞቴ አምባቢላ፣ ኮማ-አሉ ካላላ፣ ጋሌገቢታ ሞጆወርጂ፣ ኮማ-ጨራ አሉ ደረባ እና ኮማ-ሳቻኒ መስመር ያለውን መንገድ ወረዳችን ማስጠገን ይፈልጋል።
በጅማ ዞን የሊሙ ሰቃ ወረዳ መንገድና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በጅማ ዞን በሊሙ ስቃ ወረዳ መንገድና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት የገጠር መንገድ ላንጦ አለለወርቅ፣ ሞቴ አልጋ ቂልጡ ሙጃ፣ ኮማ ጨሪ አልጋ፣ ሞቴ አምባቢላ፣ ኮማ-አሉ ካላላ፣ ጋሌገቢታ ሞጆወርጂ፣ ኮማ-ጨራ አሉ ደረባ እና ኮማ-ሳቻኒ መስመር ያለውን መንገድ ወረዳችን ማስጠገን ይፈልጋል ስለዚህ በዚህ ሥራ ላይ የተሰማራችሁ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ ቀርባችሁ መወዳደር እንደምትችሉ እናሳውቃለን።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና የ2018 ዓ.ም ፍቃድ ያሳደሱ
- በማሽን ኪራይ የንግድ ፈቃድ ያለው
- የግብር መለያ ቁጥር /TIN)፡ ያለውና VAT ተመዝጋቢ የሆነ
- TOT (3%) ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ
- በማንኛውም የማሽን ብልሽት ጊዜ ባለቤቱ ባለሙያ ልኮ በራሱ ውጭ በሦስት ቀናት ውስጥ ማስጠገን የሚችል
- ተወዳዳሪዎች የማሽኑን ስም፡ የማሽኑን ሞዴል፣ ማሸኑ የተመረተበት ዘመን፤ የማሽኑ ጉልበት፤ የማሽኑ ብዛት፣ የግል ወይም ኪራይ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ከሁሉም ዋጋ 2% ብር በጥሬ /CPO/ የባንክ ቼክ ከቴክኒካል ሰነድ ማስያዝ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ አንድ አሪጅናል እና ሁለት ኮፒ በተለያየ ፖስታ አሽጎ ማስገባት አለባቸው
- የሥራ ሁኔታ ላይ ተመስርቶ ለማሽኑ የሚሠጥ ሥራ 20% ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል
- አከራዩ ማሽኖቹን የማምጣትና የመመለስ ግዴታ አለበት፣ የምግብ እና የሰርቪስ ወጪ በተወዳዳሪ ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል። የነዳጅ ወጪ ወረዳው በራሱ ወጪ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ከተወዳደሩ መሐል ሁሉንም መስፈርት አሟልቶ ዝቅተኛ ዋጋ ያስገባ ይሆናል፡፡
- የጨረታውን ሠነድ መግዣ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ) ለሊሙ ሠቃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
- የጨረታው ሠነዱ የሚሸጠው ከመስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት በሊሙ ሲቃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
- ሠነዱን የገዛ ተጫራች የገዛውን ሠነድ በተጠቀሰው መሠረት ሞልቶ እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4:30 ድረስ ብቻ የምንቀበል ይሆናል፣ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውጭ የሚመጣ ተጫራች ማስተናገድ አይቻልም፣ ጨረታው የሚከፈተው ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሠዓት ላይ ተወዳዳሪዎች/ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሊሙ ሠቃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ይሆናል ተጫራቾች ተወዳዳሪዎች/ሕጋዊ ወኪላቸው አለመገኘታቸው ጨረታው እንዳይከፈት አያደርግም፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተወዳዳሪዎች ሠነዱን ከማሸጋቸው በፊት በሕጋዊ ማህተማቸው በማረጋገጥና በሰም በታሸገ አንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0474620008/0474620146 መደወል ይችላሉ።
በጅማ ዞን የሊሙ ሰቃ ወረዳ መንገድና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት
