በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በዴቻ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ለቦባ ጐጫ ቀበሌ ሞዴል ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ ለማስገንባት ስለሚፈለግ በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በዴቻ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ለቦባ ጐጫ ቀበሌ ሞዴል ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ ለማስገንባት ስለሚፈለግ በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ፡-
- 1ኛ ደረጃ 6 BC/ GC እና ከዛ በላይ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው፤
- 2ኛ በ2017/18 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- 3ኛ የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- 4ኛ የግብር ከፋይ መለያ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- 5ኛ በ BC/ GC ግንባታ ስራ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ሁሉ በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- 6ኛ በ2016/2017 ዓ.ም በጥራት ሰርቶ ስላስረከቡት በ BC/ GC ግንባታ የመልካም ስራ አፈጻጸም ደብዳቤ ወይም የምስክር ወረቀት ያላቸው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ ብቻ ከዴቻ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ከፍለው ከመ/ቤታችን የግ/ን/አ/ስራ ሂደት መወሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የግንባታ ንግድ ፈቃድና ተያያዥ መረጃቸውን ኮፒዎችና CPO በአንድ ፖስታ የፋይናንሻል መረጃውን በአንድ ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒዎችን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 30ኛ ቀን በ8፡00 ሰዓት በዴቻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስ/ር የስራ ሂደት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በዕለቱ በታሸገበት ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- እለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ የተመሰከረ የክፍያ ማዘዣ CPO ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ቀደም ሲል ጨረታ አሸንፎ ስራውን ያስተጓጓለ /የታገደ/ ድርጅት /ተቋራጭ/ በጨረታ መሳተፍ አይችልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታ አከፋፈት ወቅት የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ሁኔታ አያስተጓጉልም፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-45-92-71-14 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ መንግስት የካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
