Tender Detail

Tender Details

  • Company የከሚሴ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት
  • Address ከሚሴ ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 033-554-0279
  • Website
  • Deadline05 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋውን 2%
  • opening date2025-11-05 00:00:00
  • Categories Water Construction Machinery And Equipment , Water Pipes And Fittings

የከሚሴ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የተለያየ መጠን ያላቸው ጋልቫናይዝድና H.D.PE ቧንቧ መገጣጠሚያ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የከሚሴ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት


 

ብሄራዊ ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የከሚሴ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የተለያየ መጠን ያላቸው ጋልቫናይዝድና H.D.PE ቧንቧ መገጣጠሚያ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ ከ250,000 /ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር በላይ ከሆኑ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በድርጅቱ የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ በCPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይንም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ሰነዳቸውን ቴክኒካል ፋይናንሻል በሚል ለይተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • በቴክኒክ ፖስታ ውስጥ የንግድ ፍቃዳቸውንና የስራ ፍቃድ፤ ቲን ነበር እና የቫት ምዝገባ መረጃዎችን በማድረግ
  • በፋይናንሻል ፖስታው በዋጋ ማቅረቢያው የእቃውን ዋጋ የተሞላበትን በማሸግ ማቅረብ ይገባቸዋል።
  1. ተጫራቾች ድርጅቱ ለመግዛት የፈለጋቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ አይነትና መጠን ናሙና ማቅረብ የሚጠበቅባቸዉ ሲሆን በእቃዎቹ ጥራትም በኮሚቴ ታይቶ የተፈለጉት እቃዎች ብቻ ለፋይናንሻል ያልፋሉ፡፡
  2. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ጨረታው ከወጣበት በ16 ቀን ጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ የሚከፈት ሲሆን በእለቱም የቴክኒካል ፖስታዎች ተከፍተው ትክከለኛ ፈቃድና ዘርፍ ለመሆኑ ብቻ ይታያል፡፡
  3. ፋይናንሻል ጨረታው የሚከፈተው በተራ ቁጥር 6 የተገለጸውን ያሟላና በናሙና ያቀረባቸው እቃዎች በቀጣዩ በቴክኒክ ኮሚቴ ጥራታቸው ታይቶ የተመረጡትን ድርጅቶች ጥሪ በማድረግና በማስታወቂያ በማሳወቅ የዋጋ ውድድሩ ይከናወናል፡፡
  4. ተጫራቾች በውድድሩ አሸናፊ ከሆነ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ለተጨማሪ ማብራሪያ ከሚሴ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ስ.ቁ 033-554-0279/201/406 በመደወል ወይም በግንባር በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  6. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የከሚሴ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት

 

Save Tender