የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምርጥ ዘር ድርጅት በ2018 ዓ.ም ከዚህ በታች የተገለጸውን የግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምርጥ ዘር ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/18 ዓ.ም
/ግዥ፣ የአገልግሎት እና ሽያጭ/፡-
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምርጥ ዘር ድርጅት በ2018 ዓ.ም ከዚህ በታች የተገለጸውን የግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1ኛ. የምርጥ ዘር መቋጠርያ ፖሊ-ባጎችን ለማሰራት
በዚሁም መሠረት፡-
- ተጫራቾች በሥራ ዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN)፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የመንግስት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ እና የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ማስያዝ ያለባቸው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ገንዘብ መጠን የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዶች ላይ የሚገለፅ በመሆኑ (በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምርጥ ዘር ድርጅት ስም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ /CPO/ ብቻ ከጨረታ ኦርጅናል ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 400 በመክፈል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምርጥ ዘር ድርጅት ዱራሜ ከተማ በሚገኘው በድርጅቱ 2ኛ ፎቅ የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 202 በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ10ኛው ቀን እስከ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ 10ኛው እና በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 202 ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን 10ኛው እና 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይከፈታል።
- ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ የጨረታ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ቀርቦ ቢገኝ ተጫራቹ ጨረታውን ከመሳተፍ ይታገዳል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ሙሉ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
ድርንቱ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር ፡- 046 554 1991 / 0465 54 21 07
ዱራሜ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምርጥ ዘር ድርጅት
