የገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 ጽህፈት መሳሪያዎች ጽዳት እቃዎች ሌሎች አላቂ እቃዎች እና ደንብ ልብሶች ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸሮች አንደኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚውሉ፡-
- ሎት 1 ጽህፈት መሳሪያዎች ጽዳት እቃዎች ሌሎች አላቂ እቃዎች እና ደንብ ልብሶች
- ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸሮች አንደኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታዉ መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው ማስረጃ(ክሊራንስ)ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15ተከታታይ የስራ ቀናት በሲንቄ ባንክ አካውንት ቁጥር 1064724141216 የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ ሎት 300.00(ሶስት መቶ ብር) ገቢ በማድረግ ከገቢዎች ባለስልጣን በተወከለው ሠራተኛ ዘወትር በስራ ሰዓት ወደ ደረሰኝ በማስቀየር ሰነዱን ከገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መውሰድ ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት በተዘጋጀዉ ሰነድ ብር 20,000(ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO ብቻ በገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ስም አዘጋጅተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚሸጡበትን ዋጋ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ በተባለው ቀን ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል። ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባችዋል እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ቫትን (15%) ያካተተ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ገቢ ማድረጊያ ቦታ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባችዋል።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች ገቢ የሚሆነው አስፈላጊውን ጥራት ማሟላቱ በባለሙያ እና በጥራት አጣሪ ኮሚቴ ሲረጋገጥ ብቻ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ ከስቶክ ወይም ከራሳቸው ስቶር መሆን ይኖርባችዋል።
- የጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት የሚሸጥ ሆኖ በ16ኛው ቀን ማለትም 29/02/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰዉ ቀን 4፡30 የሚከፈት ይሆናል።
- ከላይ የተገለጸው የመክፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
