በአራዳ ክ/ከተማ ስር የሚገኘው ቤተልሄም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሊያሰራው ለፈለገው ስራ ማለትም የቀለም ስራ፣ የፓርቲሽን ስራ፣ የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ ማፍረስና መጠገን በግንባታ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
የጥገና ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- 02/2018 ዓ.ም
በአራዳ ክ/ከተማ ስር የሚገኘው ቤተልሄም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሊያሰራው ለፈለገው ስራ ማለትም የቀለም ስራ፣ የፓርቲሽን ስራ፣ የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ ማፍረስና መጠገን በግንባታ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን የሰው ሃይል በማቅረብ የሚሰሩ እና ህጋዊ የሥራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለማሠራት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ ዶክመንታችሁን ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
- በዘርፉ የ2017/2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይመለያ ቁጥር ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- ማንኛውም ስራ ተቋራጭ ከፌዴራል ከተማ ልማት እና ኮንሰትራክሽን ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ያላቸው እና ከአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ እና ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ተመዝግቦ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ሳይዝ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ቤተልሄም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቀርበው ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው የሥራ ቀን በእለቱ ባለቤቱና ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በትምህርት ቤቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ብር 9,000 (ዘጠኝ ሺህ ብር) ማቅረብ ግዴታ አለበት። የቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ያለበት ፋይናንሻል ኦርጅናል ሰነድ ውስጥ ሲሆን የሰነዱ ወይም ከፖስታው ውጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሰሪው መ/ቤት አሸናፊው ካሸነፈበት አጠቃላይ የስራ መጠን 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይቻላል፡፡
- ተጫራች የጨረታው ፋይናንሻል ሰነድ ላይ ያልተፈረመ ሆኖ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የተስተካከለ ዋጋ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ከጨረታው ያሰርዛል። በተጨማሪም በስራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የስራ አይተም ላይ ዋጋ አለመሙላት ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በሁለት ፖስታዎች ዋና /original/ እና ኮፒ /copy/ ፖስታ ታሽጎ ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት እስከ 11ኛው የስራ ቀን በቤተልሄም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፋይናንስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 4፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጊዮርጊስ አ.አ ፖሊስ ኮሚሽን ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር፡- 011-1-11-48-00 ይደውሉ፡፡
ቤተልሄም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
