በአሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅማ ዞን የሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የግንባታ ስራ ሲከናወን እንደነበር ይታወቃል ሆኖም ግን በአሁኑ ሰዓት ኮንትራክተሩ በውሉ መሰረት የግንባታውን ስራ ባለመፈፀማቸው ወረዳው ውሉን በማቋረጥ ቀሪውን የግንባታ ስራ ግልጽ ጨረታ በማውጣት ግንባታውን ማጠናቀቅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቶል። በዚሁም መሰረት ማናቸውም በግንባታ ዘርፉ የተሰማራቹ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታማሉ ድርጅቶች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅማ ዞን የሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅማ ዞን የሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የግንባታ ስራ ሲከናወን እንደነበር ይታወቃል ሆኖም ግን በአሁኑ ሰዓት ኮንትራክተሩ በውሉ መሰረት የግንባታውን ስራ ባለመፈፀማቸው ወረዳው ውሉን በማቋረጥ ቀሪውን የግንባታ ስራ ግልጽ ጨረታ በማውጣት ግንባታውን ማጠናቀቅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቶል።
በዚሁም መሰረት ማናቸውም በግንባታ ዘርፉ የተሰማራቹ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታማሉ ድርጅቶች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።
- ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ደረጃ GC - III ወይም B II የንግድ ፋቃዳቸውን ያሳደሱ የዘመኑን ግብር የከፈሉና በጨረታ ሰነድ ላይ የቀረበውን መስፈርት የሚያሟሉ።
- ተወዳዳሪዎች በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡበትን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰረተ ቼክ CPO 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በታሸገ ፓስታ ማቅረብ የሚችሉ
- ጠቅላላ ተወዳዳሪዎች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና የፌዴራል መንግስት የተደነገገውን የግዥ ሕግ የሚያከብሩ መሆን አለባቸው።
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ ከተከፈተ በኋላ በሰነዱ ላይ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ መለወጥ ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታ መውጣት አይችሉም።
- ተወዳዳሪዎች በጨረታው ላይ መግለጫ ወይም የማሻሻያ ጥያቄ ካላቸው በተመዘገቡ በአምስት ቀን ((5) ውስጥ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስም፣ ፊርማ፣ የድርጅቱ ማህተም እና አድራሻ መጥቀስ አለባቸው።
- የጨረታውን ሰነድ በሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብና ጽ/ቤት ቁጥር 7 የማይመለስ 3000 (ሦስት ሺህ ብር) በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
- ተወዳዳሪዎች ጨረታውን ለማሰናከል ከሞከሩ ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ። ለወደፊትም በሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ በሚካሄደው በመንግስት ግንባታ ላይ አይሳተፉም። ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብም አይመለስም፡፡
- ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምር ለ21 (ሃያ አንድ ቀን) ተከታታይ የመንግስት የስራ ቀን በአየር ላይ ይውላል፡፡
- የጨረታው ሰነድ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 22ኛ የመንግስት የስራ ቀን 3:00 ሰዓት ታሽጎ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- የተሰረዘ የተደለዘ የተፋፋቀ ወይም በግልፅ የማይነበብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ መስፈርቶች በዋና በጨረታ ሰነድ ላይ ያሉ መሆናቸውን እንገልፃለን።
- አሰሪው መስሪያ ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በጥቅል የመሰረዝ መብት አለው።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅማ ዞን የሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
