የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቢሾፍቱ ለሚያስገነባው አዲስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የንድፍ ግዥ ግንባታ እና ፋይናንስ ፕሮጀክት (Design, Procurement, Construction and Financing) እና ከታች የተዘረዘሩትን ስራዎች ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን እና የግንባታ ስራ ተቋራጮችን (GC/BC/RC-1) በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የቅድመ ብቃት ግምገማ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- SSNT - T578
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቢሾፍቱ ለሚያስገነባው አዲስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የንድፍ ግዥ ግንባታ እና ፋይናንስ ፕሮጀክት (Design, Procurement, Construction and Financing) እና ከታች የተዘረዘሩትን ስራዎች ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን እና የግንባታ ስራ ተቋራጮችን (GC/BC/RC-1) በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ዋና ፋሲሊቲዎች የተርሚናል እና ኮንኮርስ (ጥቅል F1) (Main Facilities for Terminal and Concourse) (Package F1)፤
- ኤርፊልድ እና መሰረተ ልማቶች (ጥቅል I1) (Airfield and Infrastructures (Package I1)፤
- ኦፍ ሳይት ሊንክ (ጥቅል I2) (Off-Site Link (Rail and Road) (Package I2)፤
- ድጋፍ ሰጪ ፋሲሊቲዎች (ጥቅል F2) (Support Facilities) (Package F2)፤
ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ አለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ ተጫራቾች፣ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከተፈቀደለት አካል በምድብ (GC/BC/RC-1) ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ (PPPAA) የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
የቅድመ ብቃት ማመልከቻዎች በዲጂታል መንገድ ብቻ መቅረብ አለባቸው፡፡ (ፒዲኤፍ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሊስተካከሉ የሚችሉ የ Word/Excel ፋይሎችን ያካትታሉ)፤ እያንዳንዳቸው የየጥቅሉ ስም “የጥቅሉ ስም እና በቅድመ ብቃት ሰነዶች ውስጥ በተሰጡት ደህንነቱ በተጠበቀ የማስረከቢያ መመሪያዎች መሰረት እስከ ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ድረስ መላክ አለባቸው። ከዚህ የጊዜ ገደብ በኋላ የሚቀርቡ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
ሁሉም ጥያቄዎች ከማቅረቢያው ቀነ-ገደብ ቢያንስ አስር (10) የቀን መቁጠሪያ ቀናት በፊት ከዚህ በታች ወደ ተጠቀሰው አድራሻ በኢሜል ብቻ መላክ አለባቸው። መልሶች ለሁሉም ተጫራቾች ይጋራሉ፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር Tel፡- +251-1-15-17-82-58
ኢ-ሜይል:- Yodittk@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
