Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፈዴሬሽን ኃላ/የተ/ አሰላ ብቅል ፋብሪካ
  • Address አዲስ አበባ ከተማ ከጀርመን አደባባይ ወደ ሚካኤል አደባባይ በሚወስደው መንገድ ላይ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፈዴሬሽን ሕንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ወይም አሰላ- ቁሉምሳ : ኢትዮጵያ, Phone: 09-65-65-04-81
  • Website
  • Deadline06 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityለLOT 1 ብር 15,000.00፤ ለLOT 2 ብር 15,000.00፤ ለLOT 3 ብር 10,000.00፤ ለLOT 4 ብር 10,000.00፤ ለLOT 5 ብር 5,000.00፤ ለLOT 6 ብር 10,000.00፤ ለLOT 7 ብር 10,000.00
  • opening date2025-11-06 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical , Hand Tools And Workshop Equipment , Water Construction Machinery And Equipment , Water Pipes And Fittings , Mechanical Work and Materials , Metals And Metal Working , Electrical Materials

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ/የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በመጋበዝ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፈዴሬሽን ኃላ/የተ/ አሰላ ብቅል ፋብሪካ


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ/የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ፡-

  • LOT 1- Workshop Materials - NCB/OACFLTD/AMF/01/2018
  • LOT 2- Electrical Materials - NCB/OACFLTD/AMF/02/2018
  • LOT 3- Electrical and Mechanical tools - NCB/OACFLTD/AMF/03/2018
  • LOT 4- Bearing-NCB/OACFLTD/AMF/04/2018
  • LOT 5- Mechanical Seal and Oil Seal - NCB/OACFLTD/AMF/05/2018
  • LOT 6- Sheet Metals and Angle Iron - NCB/OACFLTD/AMF/06/2018
  • LOT 7- Steam Valves and pipe -NCB/OACFLTD/AMF/07/2018

ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በመጋበዝ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

  1. ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN) ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በፋብሪካችን አካውንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000257808697 ወይም በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1000043405229 በመክፈል /ገቢ በማድረግ/ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2፡00-6፡00 ሰዓት፤ ከሰዓት በኋላ 7:00-10፡00 ሰዓት ድረስ ከጀርመን አደባባይ ወደ ሚካኤል አደባባይ በሚወስደው መንገድ ላይ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ህንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ወይም አሰላ – ቁሉምሳ ከሚገኘው ፋብሪካችን ቢሮ ቁጥር 003 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በፖስታ በማሸግ አዲስ አበባ በሚገኘው የፋብሪካችን ዋና መ/ቤት ለዚሁ ተበሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ከተጠቀሰው የመዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለLOT 1 ብር 15,000.00፤ ለLOT 2 ብር 15,000.00፤ ለLOT 3 ብር 10,000.00፤ ለLOT 4 ብር 10,000.00፤ ለLOT 5 ብር 5,000.00፤ ለLOT 6 ብር 10,000.00፤ ለLOT 7 ብር 10,000.00 በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ለየብቻ በማስያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ22ኛው ቀን LOT 1 እና LOT 2 በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ላይ፤ LOT 3 እና LOT 4 በ5:00 ሰዓት ተዘግቶ በ5፡30 ሰዓት ላይ፤ LOT 5 LOT 6 እና LOT 7 ልክ በ5:40 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ 6፡10 ሰዓት ላይ ለመገኘት በሚሹ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የፋብሪካችን ዋና መ/ቤት የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ/የተ ሰባተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  6. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  7. ተጫራቾች በጨረታ ማስታወቂያና በተጫራቾች መመሪያ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነጥብ ካለና ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09-65-65-04-81/ 09-65-65-02-85 በሥራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ/የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ

 

Save Tender