Tender Detail

Tender Details

  • Company Emergency Relief Transport Enterprise (ERTE) (የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት)
  • Address አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት ትሬን ባትሪ መሸጫ ህንጻ በስተጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 439 00 75
  • Website
  • Deadline25 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Securityከሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 15%
  • opening date2025-10-25 00:00:00
  • Categories Plastic Raw Materials And Products

ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ለከባድ ተሽከርካሪ የሚውል መጠን (Size) 9*11 ተደራቢ የፕላስቲክ ሸራ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Emergency Relief Transport Enterprise (ERTE) (የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት)


 

የጨረታ መመሪያና ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ዕ/ደ/ዕ/ት/ድ/አቅ/003/18

 

ድርጅታችን በ2018 በጀት ዓመት ለከባድ ተሽከርካሪ የሚውል መጠን (Size) 9*11 ተደራቢ የፕላስቲክ ሸራ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
  2. በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የቴክኒክ ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ እንዲሁም የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ፣ የድርጅቱ ስም አድራሻ እና ማህተም በማድረግ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ከቀኑ 11፡00 ሠዓት ድረስ በአቅ/ፋ/ማ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ በግዥ የስራ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 11፡00 ሠዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሠዓት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን በድርጅቱ የስራ ቀን የማይውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ከሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 15% ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ፣ ሲፒኦ (CPO) በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ሌተር ኦፍ ክሬዲት ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ከፋይናንስ ሂ/ዳይሬክቶሬት መግዛት ይቻላል፤
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ከቫት በፊት መሆኑን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ያልተገለጸ ከሆነ ቫትን ጨምሮ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊነቱ ከተገለጸላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋው 10% ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ለከባድ ጭነት ተሽከርካሪ የሚውል መጠን (Size) 9*11 ተደራቢ የፕላስቲክ ሸራ ናሙና ከጨረታ መከፈቱ በፊት ወይም በጨረታ መክፈቻው ዕለትና ሠዓት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ለከባድ ጭነት ተሽከርካሪ የሚውል መጠን (Size) 9*11 ተደራቢ የፕላስቲክ ሸራ የሚያቀርቡትን ናሙና በአቅርቦትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት የአላቂና ቋሚ ዕቃዎች ግምጃ ቤት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ እስከ 20 ፐርሰንት ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡

ስልክ ቁጥር፡- 01 4 39 00 75/35 92/15 69/011 439 10 27

ፋክስ፡- 011 439 63 36/0114747141 ፖ.ሳ.ቁ. 2562 አዲስ አበባ መጠየቅ ይችላሉ

አድራሻ፡- ቃሊቲ ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት 70 ሜትር ገባ ብሎ

 

ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት

 

Save Tender