Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር
  • Address ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116733497
  • Website
  • Deadline23 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/
  • opening date2025-10-23 00:00:00
  • Categories Hand Tools And Workshop Equipment , Electrical Materials

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና የወርክ ሾፕ ዕቃዎች ግዥን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር


 

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር EAC 008 & 009/2018

 

  1. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና የወርክ ሾፕ ዕቃዎች ግዥን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2:30 - 6:30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7:30 -11፡00 ድረስ “ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎር አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት
  • አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ
  • አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፣
  • ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከቶ የታሸገ መሆን አለበት፡፡
  • በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ  ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም:: የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
  1. ተጫራቾች የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና የወርክ ሾፕ ዕቃዎች ግዥን የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /C.P.O/ ወይም ኮንዲሽናል ባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 208 ሲሆን፤ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ይሆናል።
  3. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  4. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልከ ቁጥር 0116676204 ፋክስ ቁጥር 0116732006 መጠቀም ይችላሉ፡፡
  5. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር

 

Save Tender