በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት ቀጥሎ ያሉትን ግዥዎች በግልጽ ጨረታ በሎት አከፋፍሎ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት ቀጥሎ ያሉትን ግዥዎች በግልጽ ጨረታ በሎት አከፋፍሎ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1 በኤሌትሪከ የሚሠራ ሞተር ሳይክል
ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃና የጽሕፈት መሣሪያ
በዚህ መሠረት፤-
1. ሕጋዊ ንግድ ፍቃድና TIN NO ቁጥር ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
3 ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ነው፡፡
4.ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይታሸግና ወዲያውኑ በዕለቱ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል።
5. VAT ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
6. ተጫራቾች ቴከኒካልና ፋይናሻል ሠነዶችን ለይተው በሁለት ፖስታ በሰም ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
7 የሚቀርበው ዋጋ ከላይ የማወዳደሪያ ሃሳብ ማቅረቢያ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት። በተጨማሪም አሸናፊው ተጫራች የከልሉ ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ በሀገርውስጥ አነስተኛ ዋጋ ላሳዩ ግዥዎች ላወጣው ጠቅላላ የውል ሁኔታዎች መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል።
8 የቀረቡ ማወዳደሪያ ሀሳቦች በተሰጠው በጊዜ ገደብ ውስጥ ጸንቶ የሚቆዩ ማስተካከያ የማይደረግላቸው መሆናቸውን እናረጋግጣለን፡
9. የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ሽያጭ 2% ከባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ማቅረብ አለባቸው፡፡
10. የጨረታ ሠነድ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር ለእያንዳንዱ ለሎት 300 ብር አጠቃላይ 600 ብር (ስድስት መቶ ብር) በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገቢዎች ቢሮ በመከፈል የጨረታ ሠነዱን ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ግዥ ፋይናንስ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 03 የከፈሉበትን ደረሰኝ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ።
11. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ከገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
ማሳሰቢያ ፤ ለበለጠ መረጃ ስልክ/ሞባይል/ቁጥር 0916020865/0916516908
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ
