በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 10 ጤና ጣቢያ ሎት የተለያዩ መድሃኒቶች እና የብራቶሪ ሪኤጀንቶች 10,000 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 10 ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 002/2018 ዓ.ም
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 10 ጤና ጣቢያ ሎት የተለያዩ መድሃኒቶች እና የብራቶሪ ሪኤጀንቶች 10,000 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ጨረታውን ለመወዳደር የምትፈልጉ ማሟላት የሚገባቸሁን መስፈርቶች
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የታደሰ ንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፣
- የመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት አለበት፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 2% ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ይውላል፡፡
- ተጫራቾች የዶክመንታቸውን ዋናውን ፎቶ ኮፒ በሶስት ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ እንደተነገራቸው ቀርበው ውላቸውን ለመፈጸም 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠው ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ለሚጠይቁ ዕቃዎች በፎቶ የዕቃውን አይነት አንዱን ዕቃ ሳንፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡበት ዋጋ ቫትን ጨምረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች መጫረት የሚችለው በተሰማራበት የስራ ዘርፍ/ በተሰጠው ፍቃድ ብቻ መሆን አለበት
- የጨረታ ሳጥን የሚዘጋው ጨረታው በወጣ 11ኛ የስራ ቀናት ጠዋት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ ኮሚቴዎች ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል።
- ተቋሙ የተሻለ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አነስተኛ እና ጥቃቅን መወዳደር የምትችሉት ከተደራጃችሁበት ወረዳ የስራ ዘርፍ እና የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ እና በምታመርቱት ምርት ብቻ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የገዛችሁትን የጨረታ ሰነድ እያንዳንዱ ላይ ማህትም ኢድርጋችሁ ለተቋሙ መመለስ አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች የምትግዙትን ሎቶች ለየብቻ አሽጋችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች በአቅራቢነት ሊስት ላይ የተመዘገበ መሆን አለበት።
- አድራሻ :- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ጤና ጣቢያ ዊንጌት አስፋው ሜዳ የስፖርት ማዘውተሪያ 200 ሜትር ገባ ብሎ ማግኘት ይቻላል፡፡
ስልክ ቁጥር 0112791077 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 10 ጤና ጣቢያ
