Tender Detail

Tender Details

  • Company የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት
  • Address በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ከብሩክ ህንፃ ፊት ለፊት ቴሌ አጠገብ ከተሰራው አዲሱ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ውስጥ 1ኛ ፎቅ ወደ ቀኝ ሲታጠፉ የወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113301548
  • Website
  • Deadline29 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Security60,000 /ስልሳ ሺህ ብር/
  • opening date2025-10-29 00:00:00
  • Categories Electronics Materials , Camera

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለከተማው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ማለትም የደኅንነት ካሜራ እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ ለመፈፀም በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ባላቸው አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር-003/2018

 

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለከተማው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ማለትም የደኅንነት ካሜራ እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ ለመፈፀም በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ባላቸው አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ስለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NUMBER/ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች በኦን ላየን ምዝገባ (eGP) በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው የእውቅና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ፤ CPO 60,000 ብር በማሠራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከወ/ጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ግ/ን/አስ/ዋና/ሥራ/ሂደት ክፍል ቀርቦ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  6. ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ሁለት ኮፒውን በተናጠል ለይቶ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. መ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊ ተወዳዳሪ የሚለየው ተወዳዳሪዎች ለእያንዳንዱ ነጠላ እቃ ባቀረቡት ዋጋ መሠረት የቀረበ አነስተኛ ዋጋ ወይም በጥቅል ሎት የተሻለውን የጨረታ አሸናፊ የመለየት ሥራ ሊሠራ ይችላል፡፡
  • ማሳሰቢያ ፅ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
  • በጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው ከመከፈት እያስተጓጉልም፡፡
  • መ/ቤቱ ከሸጠው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ ሞልቶ መወዳደር አይቻልም፡፡
  • የጨረታ ማስታወቂያውንና የጨረታ ሰነዱ የሚጠይቀውን ዝቅተኛ መስፈርት የማያሟሉ ተጫራቾች ወይም አቅራቢዎች ከጨረታው ውጪ ይደረጋሉ፡፡
  • የጨረታውን መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ብሔራዊ የሕዝብ በዓል ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የሥራ ቀን ይተላለፋል፡፡

ለበለጠ መረጃ አድራሻ፡- በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ከብሩክ ህንፃ ፊት ለፊት ቴሌ አጠገብ ከተሠራው አዲሱ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሕንፃ ውስጥ 1ኛ ፎቅ ወደ ቀኝ ሲታጠፉ የወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0113301548/0911921780/ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡

 

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender