Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
  • Address ሀዋሳ ከተማ አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-212-13-34
  • Website
  • Deadline24 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Security10,000 (አስር ሺህ ብር)
  • opening date2025-10-24 00:00:00
  • Categories Gardening And Landscaping

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ለሚያለማው አረንጓዴ ልማት እንክብካቤ ስራ ከሎት 040/2018 እስከ ሎት 148/2018 ድረስ ያሎት 109 ሎቶች ለማሰራት ያስፈለገ በመሆኑ በተዘጋጀው ዲዛይን መሠረት በዘርፉ ከተደራጁ ማህበራት መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ለሚያለማው አረንጓዴ ልማት እንክብካቤ ስራ ከሎት 040/2018 እስከ ሎት 148/2018 ድረስ ያሎት 109 ሎቶች ለማሰራት ያስፈለገ በመሆኑ በተዘጋጀው ዲዛይን መሠረት በዘርፉ ከተደራጁ ማህበራት መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማህበራት መወዳደር ይችላሉ።

  1. በአረንጓዴ ልማት ተደራጅቶ ፍቃድ ያላቸው ማህበራት፤
  2. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤
  4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፣
  5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 (ሃያ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ወስዶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
  7. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዘ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ ተከታታይ ቀናት በፋይ ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው በ11ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት 4፡30 ሠዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች በሲዳማ ክልል እና ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ተመሳሳይ ሥራ በእጁ ላይ ካለና የሥራው አፈጻጸም 70% ካልደረሰ በጨረታ መወዳደር አይችልም፡፡ ሥራው 70% እና በላይ የደረሰ ከሆነ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  10. በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲክ ቼክ በሚደረግበት ጊዜ በሁለቱ መካከል ከ5% (ከአምስት ፐርሰንት) በላይ ሆነ በታች ልዩነት ካለ ተጫራቹ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
  11. ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ላይ ከአሥራ አምስት ፐርሠንት (15%) በላይ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
  12. ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ታች (ከ20%-30%) ከሃያ እስከ ሰላሳ ፐርሠንት በታች መውረድ የለበትም፡፡
  13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ስልክ ቁጥር 046-220-99-63/046-212-13-34

 

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ

 

Save Tender