Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጎለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ከአ/አበባ በስተ ሰሜን 110 ኪ/ሜ ርቀት በደብረብርሃን መስመር ላይ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-6-32-01-47
  • Website
  • Deadline29 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-10-29 00:00:00
  • Categories Agriculture And Farming , Gardening And Landscaping , Flora And Horticulture

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት የተለያዩ የደን ዘር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጎለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:- 04/2018

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት የተለያዩ የደን ዘር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የምትፈልጉ፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ በዘመኑ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN No/ ያላቸውና ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ዋጋ ባላቸው ግዥዎች የሚሳተፉ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ እና ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. የደን ዘሩ በአንድ ጊዜ በአይነት፣ በመጠንና በጥራት ሳያጓድል ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ አድራሻቸውንና ፈርማቸውን ማስፈር አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ፤ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋና እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር አፍ ክሬዲት ወይም ገ/ዋና ጽ/ቤት በመሂ1 ያስያዙበትን ደረሰኝ ከኦሪጅናል ዋጋ ማቅረቢያ ውስጥ መያያዝ አለበት። የእቃ ግዥው መ/ቤቱን፣ የተጫራቾችን ስምና አድራሻ፣ እንዲሁም የግዥውን አይነት በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው በዚሁ ዕለት በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ይታሸግና በዕለቱ በ8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።
  7. 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው በመንግሥት የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  8. መ/ቤቱ ጨረታውን በሎት ያወዳድራል፡፡
  9. ተጫራቾች የእቃውን አይነትም ሆነ መጠን በጨረታው በሙሉ ወይንም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ሆኖም አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት ከሎት ማጉደል አይችሉም፡፡
  10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት አን/ጠ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ጫጫ ከተማ ድረስ በየንብረት ክፍሉ ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ በሚሆኑበት ጊዜ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ውል ከመግባቱ በፊት ናሙና ይዘው መቅረብ አለባቸው።
  12. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፀ በተጫራቾች መመሪያ እና በኦሪጅናል ሰነዱ ላይ በዝርዝር ስለሚገለጽ ዝርዝራቸውን በትኩረት ማየት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  13. በማንኛውም ግዥ ለእቃዎች ከብር 20,000 /ሃያ ሺህ/ እና ለአገልግሎት ከብር 10,000 /አስር ሺህ/ በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈጸምለት ክፍያ ላይ 3% ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡
  14. ተጫራቾች በሞሉት ዋጋ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ማድረግና በፍሉድ መደለዝ አይፈቀድም፡፡ ምንአልባት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ ስህተት ቢፈጠር አንድ ሰረዝ አድርጐ ስለመሰረዙ መፈረም አለበት፡፡
  15. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  16. ጽ/ቤቱ የሚገኘው ከአ/አበባ በስተሰሜን 110 ኪ/ሜ ርቀት በደብረብርሃን መስመር ላይ ነው፡፡
  17. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር:- 011-6-32-01-47 ደውለው ይጠይቁ፡፡

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender