Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ኢት/ያ ከልል ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


                                                                ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 

በደቡብ ኢት/ያ ከልል ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 8 የቤትና የቢሮ እቃዎች (Furniture)፣ ሎት 9. የሞተር ሳይክል ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፣ 

  1. በጨረታ መሳተፍ የሚችሉት በሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች በአቅራቢነት የተመዘገቡና ለ2018 በጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ ከዚህ በፊት ላከናወኗቸው ተመሳሳይ ሥራዎች /አገልግሎቶች/ ከአሠሪው አካል የመልካም ሥራ ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡ 

  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት (አስራ አምስት ቀናት) ከታች ከተጠቀሰው አድራሻ መግዛት ይችላሉ፡፡ 

  3. የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 400.00 (አራት መቶ ብር) በማቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ሥራ ሂደት ቢሮ ይገኛል፡፡ 

  4.  ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 (አራት ሰዓት) ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ዘገይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል፡፡ 

  5. ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ሌሎች መገኘት የሚፈልጉ ባሉበት በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ 16ኛው ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ (የሥራ ቀን ካልሆነ) በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ 

  6.  ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ለሎት 8 – 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/፤ ለሎት 9 - 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረለት ሲፒአ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ 

  7. ርከብክብ የሚፈጸምበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳዳር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይሆናል፡፡ 

  8. የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

          ለበለጠ መረጃ:- 046-1-80-08-63 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ 

                                   በደቡብ ኢት/ያ ክልል መንግስት ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ

Save Tender