ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተማሪዎች መማርማስተማር አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ኬሚካሎችና አፓራተሶች (ኬሚካሎች (Different Chemicals) የባዮሎጂ መሳሪያዎች (Biology Apparatus) ፣ የኬሚስትሪ መሳሪያዎች (Chemistry Apparatus) እና የፊዚክስ መሳሪያዎች (Physics Apparatus) በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተቀመጠው ዓይነትና ብዛት መሰረት በግልጽ ጨረታ በዘርፉ የተሰማሩት ድርጅቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር:-NCB/OEB/GOV/01/2018
ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተማሪዎች መማርማስተማር አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ኬሚካሎችና አፓራተሶች (ኬሚካሎች (Different Chemicals) የባዮሎጂ መሳሪያዎች (Biology Apparatus) ፣ የኬሚስትሪ መሳሪያዎች (Chemistry Apparatus) እና የፊዚክስ መሳሪያዎች (Physics Apparatus) በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተቀመጠው ዓይነትና ብዛት መሰረት በግልጽ ጨረታ በዘርፉ የተሰማሩት ድርጅቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ፣ ቁጥር (TIN)፣ የግብር ክፍያ ማስረጃ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ማስረጃ፣ የጨረታ ተሳትፎ ደብዳቤ (Clearance) ማስረጃ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
-
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ አንደኛ ፎቅ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በአሮሚያ ትምህርት ቢሮ ንግድ ባንከ ቁጥር 1000007342121 'Oromia Education Bureau' ስም በመከፈልና የባንክ ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሠነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
-
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ጋራንቲ (Bid Bond) ወይም CPO በሁኔታ ላይያልተመሠረተ (Un conditional Bank Guarantee) ብር 100,000.00( አንድ መቶ ሺህ) በኦሮሚያ ት/ቢሮ ስም የተዘጋጀ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረበ ይኖርባቸዋል።
-
- ተጫራቾች ኬሚካሎቹን /አፓራተሶቹን/ ዝርዝር ነጠላ ዋጋ እና ከቫት ጋር ከጨረታው ሰነዱ ውስጥ በተገለጸው ስፔስፍኬሽን መሠረት በመሙላትና የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በሁሉም ገፆች ላይ በማሳረፍ ፋይናንሻል ኦሪጂናል፣ ቴከኒካል ኦሪጂናል፣ ፋይናንሻል ኮፒ ፣ቴክኒካል ኮፒ እና C.P.O ወይም ባንክ ጋራንት ለየብቻ በፖስታ ከታሸገ በኋላ በአንድ ላይ በፖስታ ታሽጎ ሳር ቤት ወረድ ብሎ በሚገኘው የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 3ኛ ፎቅ በሥራ ሰዓት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
-
- ተጫራቾች የኬሚካሎቹን/ የአፓራተሶቹን/ ዓይነት እና ብዛት ላይ ሙሉ በሙሉ መሳተፍ አለባቸው በተጨማሪም አሸናፊው ድርጅት እቃዎቹን ገላን ከተማ በሚገኘው የኦሮሚያ ትምሀርት ቢሮ ንብረት ከፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና C.P.O ወይም በባንከ ጋራንት ያሲዛል።
-
- ተጫራቾች ሙሉ አድራሻቸውን ስልክ ቁጥራቸውንና የጨረታ ቁጥሩን በፖስታ ላይ በመጥቀስ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ይህ ቀን የመንግሥት የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የመንግሥት የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
-
- ቢሮው የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው::
አድራሻ፡- የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ፣ ሳርቤት ኦሮሚያ ቢሮዎች ግቢ ውስጥ
ስ.ቁ 0113717973
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ
