Tender Detail

Tender Details

  • Company ሳህሌ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  • Address ቦሌ ኬኬር : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-35-98-83-02
  • Website
  • Deadline28 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-10-28 00:00:00
  • Categories Ict Equipment'S And Its Accessories , Furniture

ድርጅታችን ሳህሌ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በድርጅቱ መጋዘኖች የሚገኙ አዳዲስና መጠነኛ ጉዳት ያለባቸው እቃዎቸች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ሳህሌ ኃ/የተ/የግ/ማህበር


ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ የቤትና የቢሮ ፈርኒቸር ፣የአዳራሽና የላይብረሪ

መገልገያዎችና መጋረጃ የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ሳህሌ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በድርጅቱ መጋዘኖች የሚገኙ አዳዲስና መጠነኛ ጉዳት ያለባቸው፡-

1. የቤት ውስጥ ቁሳቁስ ባር ቡፌ የምግብ ጠረጳዛ የልጆች አልጋ ቁምሳጥን ሶፋ

2. የትምህርት ቤት እና የላይብረሪ ቁሳቁሶች፡- የመጽሐፍትና የመጽሔት መደርደሪያ የጥናት ጠረጴዛ የተማሪ ወንበር ማስታወቂያ ቦርድ ግርን/ኋይት ቦርድ ድሮዊንግ ጠረጴዛ

3. የቢሮ ቁሳቁሶች፣ የቡና፣የጽሕፈት፣የኮምፒውተር፣የስብሰባ ጠረጴዛዎች፤ ፋይል ካቢኔት ሎከር እና የተለያዩ የቢሮና የአዳራሽ ወንበሮች

4. ሌሎች፡- የእንግዳ መቀበያ ዴስክና ቨርቲካል መጋረጃ ከነአክሰሰሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፥ በዚህ መሰረት ማንኛውም ተጫራች

  • ይህ ጨረታ በጋዜጣ ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ ከ2፡30-11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ ከ2፡30-8፡00 ሰዓት ቦሌ ኬኬር 2ኛ ወለል ላይ ከሚገኘው የድርጅታችን ቢሮ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታው ዶክመንት መግዛት ይችላሉ፡፡
  • በመጋዘን የሚገኙ ዕቃዎችን ማየት የሚፈልግ የጨረታ ዶክመንት ግዢ የፈፀመ ተጫራች ፅቃዎቹን ከጨረታው መክፈቻ አንድ ቀን ቀደም ብሎ እስካለው ቀን ድረስ በድርጅቱ ማሳያ ወይም መጋዘን ተገኝቶ መመልከት ይችላል፣
  •  ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፣
  • ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ዶክመንት ላይ ብቻ በመሙላት ማህተምና የህጋዊ ወኪላቸውን ፊርማ በማሳረፍ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • የጨረታ ዋጋውን አንድ በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
  • ዋጋ የተሞላበትን የጨረታ ዶክመንት የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ድርጅት ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላል፡፡
  • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፣ የጨረታ መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ ወይም የሥራ ቀን የማይሆን ከሆነ በቀጣይ ባለው የሥራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • አሸናፊ የሆነው ተጫራች አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ ባሉት ሰባት ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን የጨረታ ዋጋ ሙሉ ለሙሉ ከፍሎ አሸናፊ የሆነበትን ዕቃዎች ከድርጅቱ መጋዘን ማንሳት አለበት፣
  • በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ዕቃዎቹን ሙሉ ለሙሉ የማያነሳ ከሆነ ግን ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ወደ ድርጅቱ ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡

አድራሻ፡- ቦሌ ኬኬር፣ ስልክ ቁጥር 09-35-98-83-02

ሳህሌ ኃ/የተ/የግ ማህበር

Save Tender