Tender Detail

Tender Details


የደጎሎ ከተማ መ/ ውሃ / ፍሳ / አገ / ድርጅት የተለያዩ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የደጎሎ ከተማ መ/ ውሃ / ፍሳ / አገ / ድርጅት


የጨረታ ማስታወቂያ

የደጎሎ ከተማ መ/ ውሃ / ፍሳ / አገ / ድርጅት የተለያዩ ዕቃዎች ግዥ ጨረታ ሰነድ መመሪያ

ሎት1 የፅህፈት መሳሪያና የጽዳት እቃዎች

ሎት2 የቧንቧ መገጣጠሚያና ቧንቧ ቆጣሪ

ሎት3 የደንብ ልብስ

ሎት 4 የግንባታ ማቴሪያሎች

ሎት5 የተለያዩ ኤሌክትሮኒከስ እና የኤሌከትሪከ ማቴሪያሎች የ2018ዓም በጀት ዓመት

ለቢሮ አገ/ት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ማንኛውም ድርጅት በጨረታው መሳተፍ ይቻላል።

1/ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው

2/ የዘመኑን ግብር የከፈለና የቲን ነበር ተመዝጋቢ የሆነ

3/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክርወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4/ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ _ ከላይ ከተ/ቁ 1 እስከ 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ።

5/ ተጫራቾች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ላይ የተቀመጡትን ዝርዝር ዋጋ በትከክል ማስቀመጥ አለባቸው ስርዝ ድልዝ ያለው በመ/ቤቱ ተቀባይነት የለውም ።

6/ በጨፈታው ለመሳተፍ የሚያስፍልገውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር / በመከፈል ከደጎሎ ከተማ መ/ውሃ/ ፍሳ / አገ / ድርጅት ከቢሮ ቀጥር 3 መግዛት ይቻላል።

7/ የዋጋ ማቅረቢያ መረጃ አሟልቶ በእያንዳንዱ በፖስታ አብሮ በማሸግ እያንዳንዳቸው ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ስም ፊርማ ማህተም በማድረግ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡

8/ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1%ፐርሰንት በባንከ የተረጋገጠ ከፍያ /ሲፒኦ / ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ መሂ አንድ ማስያዝ ያለባቸውና የአሸናፊነት ደብዳቤ በደረሳቸው በ5 የሥራ ተከታታይቀናት ውስጥ ውል መወሰድ አለባቸው።

9/ ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ16 ቀን 4፡00 ይዘጋና በዚያው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት 4፡ 30 ይከፈታል። ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

10.መ/ቤቱ በጨረታው የሚገዙ እቃዎች ላይ 20% ጨምሮና ቀንሶ መግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11/ ማንኛውም ተጫራች ግዥው በጥቅል /ሎት/ መሆኑን አውቆ ለእያንዳንዱ እቃ ዝርዝር ዋጋ መሙላት ይኖርበታል። የተዘረዘሩ እቃዎችን በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይሆናል።እንዲሁም አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፋቸውን እቃዎች ሙሉ በሙሉ ገቢ ካላደረጉ ከፍያ የማይፈጸም መሆኑ ይታወቅ።

12/ናሙና መቅረብ ያለባቸው እቃዎችን አሸናፊው ተጫራች ውል ከመውሰዱ በፊት ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅበታል።

13/ አሸናፊው ተጫራች ውል በወሰደ በአንድ ሳምንት ውስጥ እቃውን ገቢ አድርጎ ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል፣ ለሥራው የሚያስፈልጉ የቀን የጉልበት ሠራተኞችንም ማመቻት አለበት፡፡

 

14/ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል /በሙሉ/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

15.በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው መረጃ ከፈለጉ

 

በስልክቁጥር/0935254747/0919971520/ 0943745858 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የደጎሎ ከተማ መጠጥ ውሃ ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

Save Tender