Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian sugar industry group Omo kuraz 1 & 3 Sugar Factory (በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት)
  • Address አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል በሚያስገባው አስፓልት ከጦር ሃይሎች ወደ ዘነበ ወርቅ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ 3 ቁጥር ማዞሪያ / ቶታል ገባ ብሎ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ላይ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 251910120628
  • Website
  • Deadline20 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-10-20 00:00:00
  • Categories Printing And Publishing

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት የተለያዩ ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ የህትመት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian sugar industry group Omo kuraz 1 & 3 Sugar Factory (በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት)


ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:- LP/OT/022/0KSF1 & 8/2018

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት የተለያዩ ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ የህትመት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ስነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ አዲስ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት፣ በተጨማሪም ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን/መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ/መረጃ ማቅረብ አለባቸው ::

2. ተጫራጮች የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚመለከተው አድራሻ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00፣ ከሰዓት ከ7፡00-10:30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ ገዝተው በጫረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ

ግዥ ቡድን (ማስተባበርያ ቢሮ)

 አድራሻ፡- ኮልፌ ቀራኒዮ

ከጦር ሃይሎች ወደ ዘነበ ወርቅ በሚወስደው መንገድ

በተለምዶ 3 ቁጥር ማዞርያ / ቶታል ገባ ብሎ

የፈዴራል ቤቶች ኮርፖረሽን ህንፃ ላይ

ሕ -5 ቢሮ ቁጥር 1371/125 ፎቅ

የስልክ ቁጥር (አድራሻ) +251-963442882/+251-910120628/251-916170834

አዲስ አበባ

3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ህትመት የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታዎች ላይያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል:

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡ በጨረታው መከፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው 10/2/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 10/2/ 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡

5. የጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው ::

6. የጨረታው ማስረከቢያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ ለ 60 ቀናት ነው፡፡

ፋብርካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩብ የኦሞ ኩራዝ 1 ና 3 ስኳር

ፋብሪካ ጽ/ቤት

Save Tender