Tender Detail

Tender Details

  • Company በቄለም ወለጋ ዞን የየማሎጊ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ቄለምወለጋዞን የማሎጊ ወለል ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ተጆ : ኦሮሚያ ክልል : ኢትዮጵያ, Phone: 09-10-31-08-20
  • Website
  • Deadline31 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security10,000.00
  • opening date2025-11-01 00:00:00
  • Categories Office Equipment

በቄለም ወለጋ ዞን የየማሎሚ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት በወረው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለሚገዙ ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን እንዲሁም የደንብ ልብስ ለመግዛት የወጣ የጨረታ ደንብ እና መመሪያ አንደሚከተለው ተዘርዝሯል፡፡

በቄለም ወለጋ ዞን የየማሎጊ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በቄለም ወለጋ ዞን የየማሎሚ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት በወረው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለሚገዙ ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን እንዲሁም የደንብ ልብስ ለመግዛት የወጣ የጨረታ ደንብ እና መመሪያ አንደሚከተለው ተዘርዝሯል፡፡

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የ2017 የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ ወይም /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

3. በገ/ኢ/ት ሚንስቴር ባቅራቢዎች የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታው ተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉት ዕቃ በምን በምን አይነት እቃዎች ላይ መሆኑን ለይተው መግለፅ አለባቸው፡፡

5. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ሁኔታዎችን መለወጥ ወይም ማሻሻል ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይቻልም፡፡

6. መስሪያ ቤቱ የሚገዛውን አቃዎች ብዛት እንደአስፈላጊነታቸው በሙሉ ወይም በከፊል ማዘዝ ይችላል።

7. የሚቀርቡት እቃዎች በተሰጠው አስፕስፊኬሽን ካልቀረቡና ማንኛውም አይነት ስህተት ቢፈፀም ሃላፊነቱ የአቅራቢው ይሆናል።

8. ጨረታው የሚካሄደው የድርጅቱን የገበያ ጥናት ማዕከል የማድረግ ሲሆን ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች አይነት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቹ ያንዱን ዕቃ ዋጋ በቁጥርና በፊደል መፃፍ አለበት። በቁጥርና በፊደል በተፃፈ መካከል ልዩነት ቢኖር በፊደል የተጻፈው ይወሰዳል፡፡

9. አቅራቢው ድርጅት እቃዎችን ቄለም ወለጋ ዞን በየማሎጊ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ አለባቸው፡፡

10. ተጫራቾች ላሸነፉባቸው እቃዎች ከመስሪያቤቱ ጋር ውል መግባት አለባቸው፡፡

11. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ 10000 (አሥር ሺህ) ብር ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል

12. አሸናፊዎች በሚገቡት ውል መሰረት ለመፈጸም ለውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ላይ10% በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ለውል ማስከበሪያ የተያዘ ሲፒኦ በውሉ መሰረት እስኪፈጸም ተይዞ ይቆያል፡፡

13. ስምምነት ያስያዙት ገንዘብ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡

14. ተጫራቾች በሰነዳቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ገልጸው መፈረም አለባቸው፡፡

15. የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ) የሌለው ሆኖ በጉልህ የሚታይ መሆን አለበት፡፡

16. ከተጠየቀው ብዛት አሳንሶ ማቅረብ አይቻልም።

17. ተጫራቶች ከጨረታው መክፈቻ እለት ጀምሮ ያቀረቡት ዋጋ የሚቆይበት ጊዜ አጠናቀው/validty date/ ኢቃውን የሚያስገቡበትን ቀን መግለፅ አለባቸው፡፡

18. አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

19. ተጫራቶች መሸነፋቸው እንደተረጋገጠ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያው ይመለስላቸዋል

20. ተጫራቾች ከሽያጭ በኃላ የሚሰጡት አገልግሎት (after sales service) መግለፅ ይኖርባቸዋል፡

21. ዋጋው መሞላት ያለበት መ/ቤቱ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ ብቻ ነው፡፡

22. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ 21 ተከታታይ ቀናቶች አየር ላይ ውሎ በዚሁ ቀን በ11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ ከጠዋቱ 2፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል

23. በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የጨረታ ሰነድ በማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) ከየማሎሚ ወለል ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት መግዛት ይችላል።

24. ተጫራቾች የቴከኒክና የዋጋ ፖስታ ለየብቻ ወይም በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለባቸው፡፡

25. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ዋጋ ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለበት፡፡ወይም የሚያቀርበው ዋጋው ከቫት ጋር መሆን አለበት፡፡

26. ማንኛውም ተጫራች መ/ቤቱ የፈለጋቸውን ዕቃ ያንዱን ዋጋ መሙላት አለበት፡፡ሞልቶ ካልተገኘ የሌላ ተጫራች ትልቁ ዋጋ ይደመርበታል፡፡ ጨረታው የሚገመገመው የመ/ቤቱ የገቢያ ጥናትን ማዕከል ያደረገ ሲሆን ከገበያ ጥናቱ 10 ከፍ ያለ ዋጋ ወይንም ዝቅ ያለ ዋጋ ውድቅ ይደረግና የገበያው የዕቃው የተጠና ዋጋ ይደመርበታል፡፡

27. በቄለም ወለጋ ዞን የየማሎሚ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ተጆ ከተማ የጨረታው ሰነድ ስለሚገኝ መጥቶ መግዛት ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ፡ -የመ/ቤታችን የግዥ መጠን በ20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።

መ/ቤታችን የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡

አድራሻ፦ ቄለም ወለጋ ዞን የማሎ ጊ, ወለል ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ተጆ

ስልክ ቁጥር: - 0910310820/0917369084

በቄለም ወለጋ ዞን የየማሎጊ 7 ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender