በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለደጀን ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በአልማ በጀት የትኖራ ቀበሌ የቅድመ መደበኛ /አጸደ ህጻናት/ የመማሪያ ክፍል ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት
የግንባታ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለደጀን ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በአልማ በጀት የትኖራ ቀበሌ የቅድመ መደበኛ /አጸደ ህጻናት/ የመማሪያ ክፍል ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋበዛል፡፡
- በዘርፉ የተሰማራ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለውና ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- በግንባታ ስራ ደረጃ 7 GC/BC እና ከዚያ በላይ የሆነና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ካደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤና የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ/ የግዥው መጠን /ከ200,000/ ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር1-5 የተዘረዘሩትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የግንባታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጨረታ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የተጠየቀውን የትምህርት ቤት ግንባታ ስራ በጥራት መስራትና ማስረከብ አለባቸው
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመፈረምና የድርጅቱን አድረሻ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመፈረም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ31ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3:30 ድረስ በመ/ቤቱ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ እለት 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ዝግ /በአል/ የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታው ተሳታፊዎች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0587760443 መደወል ይቻላል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
