ፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/ኅ/ስራ ማህበር የተለያዩ ስራዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/ኅ/ስራ ማህበር የተለያዩ ስራዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
|
ሎት 1
|
አስ ቢውልት ዲዛይን (3,613 ካ.ሜ እና 1,828 ካ.ሜ ስፋት ያላቸው ቦታዎች)
|
|
ሎት 2
|
የአዋጭነት ጥናት
|
ተጫራቹ ማሟላት ያለባቸው፦
- ለሎት 1 በህንፃ አማካሪ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣
- ለሎት 2 በገበያ አዋጭነት ጥናት ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸዉ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ሰርቲፊኬት ያላቸዉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ያላቸዉ፣
- የዘመኑን ግብር መክፈሉን የሚያረጋግጥ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን የስራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ለሎት 1 የአማካሪ ደረጃ 1 ብቃት ማረጋገጫ ሰርትፊኬት ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቹ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለሚሰጠው ዋጋ 2% በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስገባት ይኖርበታል።
- ለሎት 1 አሸናፊው አማካሪ ድርጅት የሰራውን አስ ቢውልት ዲዛይን ከሚመለከተው አካል (ክፍለ ከተማ) ማፀደቅ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከሻላ መናፈሻ የሰው ሃይል አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበት ፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ እንዲሁም አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ቴክኒካል ሰነድ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን ጨረታው በ6ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ +251919446865 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።
የፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/ኅ/ስራ ማህበር
