በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ ደረጃውን የጠበቀ ለጥሬ ዘር መቋጠሪያ ሶተሌ (Sisal String) እና ለተበጠረ ዘር መስፊያ ከር (Clean Seed Yam) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል ፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
መስፊያ ክር እና ሶተሌ ግዥ
የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ - ምዘአዘ/ግጨ/02 ሠነድ/2018
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ ደረጃውን የጠበቀ ለጥሬ ዘር መቋጠሪያ ሶተሌ (Sisal String) እና ለተበጠረ ዘር መስፊያ ከር (Clean Seed Yam) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል ፡፡ በዚሁ መሠረት፡-
1.ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስከር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት፣ በጨረታ በመሳተፍ የሚሰጥ የምስከር ወረቀት (ከሊራንስ) ኮፒ ማቅረብ የሚችል እና በመንግሥት የግዥ መመሪያ መሠረት በመንግሥት የግዥ አቅርቦት የተመዘገበ መሆን አለበት፡፡
2.ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% ሆኖ ከ2,000,000.00 (ሁለት ሚሊዮን ብር) ያልበለጠ በምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ (Seed Supply Sector) ስም የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ በC.P.O ዋስትና ማስያዝ ያለበት ሲሆን የጨረታው ዋጋ ለ30 (ሰላሳ) ቀናት የፀና መሆን አለበት፡፡
3.ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠዋት ከ2፡00 - 6፡00 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡00 - 10:30 ቃሊቲ ጉምሩከ ፊት ለፊት በሚገኘው በምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4 የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
4.ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
5.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል፣ ፋይናንሻል እና CPO በተናጠል ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያዬ ፖስታ ውስጥ አስገብቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡
6.ጨረታው ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ጨረታው ይከፈታል፡፡
7.መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 011 6 18 61 25 አዲስ አበባ
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ
