በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 12 የኮልፌ ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት ዓመት ለሰራተኞቹ የመስተንግዶ ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የካፍቴሪያ የመስተንግዶ/የአገልግሎት ግዥ ጨረታ 5000 (አምስት ሺ ብር ብቻ) ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት ሎቶች መሠረት የምትችሉ / ከህጋዊ አቅራቢዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ኮልፌ ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የመለያ ቁጥር ኮ/ጤ/ጣ 02/311/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 12 የኮልፌ ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት ዓመት ለሰራተኞቹ የመስተንግዶ ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የካፍቴሪያ የመስተንግዶ/የአገልግሎት ግዥ ጨረታ 5000 (አምስት ሺ ብር ብቻ) ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት ሎቶች መሠረት የምትችሉ / ከህጋዊ አቅራቢዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በዚሁም መሰረት ከታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟሉ አቅራቢዎች በዚህ ጨረታ መሳተፍ ይችላሉ
- ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ፡ በኢትዮጵያ የግብር ህጎች በተደነገገው መሰረት የግብርና የታክስ ግዴታ መወጣትን የሚያመለክቱ ሰነዶች የአቅራቢዎች ዝርዝር ምዝገባ የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች መሆን አለባቸው
- የጨረታውን ሙሉ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 12ኮልፌ ጤና ጣቢያ ግዥ ቡድን ቢሮቁጥር 80 አራተኛ ፎቅ መግዛት ትችላላችሁ
- ማንኛውም ተጫራች የገዛውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ በተጫራች መሞላት ያለበትን ክፍሎች በሙሉ የመሙላት እና ሙሉውን ሰነድ ማስገባት ይኖርበታል ይህን ያላደረገ ተጫራች በቅድመ ጨረታ ልየታ ውድቅ እንደሚሆን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች የመጫራቻ ሰነዳቸውን በማዘጋጀት ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒውን ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እስከ 10 (አስረኛው) ተከታታይ የስራ ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ-በፖስታ በማሸግ ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ዋጋ ማቅረቢያውን ከመሙላታቹ በፊት ተቋሙ ለሰራተኞቹ የመስተንግዶ ዋጋ ተመጣጣኝ እንዲሆን ሲባል የውሃ የመብራት የቤት ኪራይ የተለያዩ የካፍቴሪያ ዕቃዎች ሌሎችም ድጎማዎች ስላሉት ማየት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በጋዜጣ ከወጣ ጀምሮ በተከታታይ የስራ ቀን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ወዲያው 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጤና ጣቢያው የስብሰባ አዳራሽ አራተኛ ፎቅ ይከፈታል።
- የጨረታ መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ላይ ያልሆነ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ከላይ በየሎቱ በ0.5 ፕርሰንት ተሰልቶ የተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ የብር መጠን CPO በባንክ በተረጋገጠ/ሲፒኦ/ብቻ በማስያዝ ደረሰኙን በ ሰነድ ውስጥ አብረው በማካተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት የሞከረ እንደሆነ ከጨረታው የሚሰረዝ እና ለወደፊቱም በመንግስት ግዥ ጨረታ አንዳይሳተፉየሚደረግ ሲሆን ያስያዘውም የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን አሸናፊነት ከተገለፀ ከ7 የቅሬታ ቀናት በኋላ ቀርበው ውል ካልፈፀሙ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- በምግብ እና በመጠጥ በጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ የተደራጁበትን ፍቃድ እና አስፈላጊውን ዶክመንት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋ ከመሙላታቸው በፊት የካፍቴሪያውን ሁኔታ ማየት ይኖርባችዋል ይህ የመስተንግዶ ጨረታ ለተቋሙ ሰራተኞች መንግስት በአነስተኛ ዋጋ የምግብ አቅርቦት እንዲያገኙ በመፈለጉ ጭምር ነው የተለያዩ አስተያየቶች የተደረጉት ፤
- አሸናፊው ተጫራች የመስተንግዶ አቅርቦት ከሰኞ እስከ እሁድ ማታም ቀንም በባአላትም እንዲሁም ተቋሙ ልዩ ፕሮግራሞች ሲኖሩት ባልተቆራረጠ መንገድ ማቅረብ ይኖርበታል።
- መስሪያ ቤቱ የሚገዙ ዕቃዎችና ተያያዥ አገልግሎቶች መጠን ሊጨመር ወይም ሊቀንስ የሚችልበት መቶኛ 20%
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ወረዳ 12 የኮልፌ ጤና ጣቢያ ኮልፌ አጠና ተራ ከፖሊስ ጣቢያው ከፍ ብሎ
አድራሻ ፡- አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ
ስልክ ቁጥር፡_ 011 273-88-55 011-280-10-21 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ኮልፌ ጤና ጣቢያ
