የመከላከያ ኮንስትራከሽን ኢንተርፕራይዝ ለዋና መ/ቤት ጥገና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የማሽን መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም ተጫራቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/SP/146/2025
የመከላከያ ኮንስትራከሽን ኢንተርፕራይዝ ለዋና መ/ቤት ጥገና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የማሽን መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም ተጫራቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃውን አይነት |
የፕሮጀከት ስም |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ
|
|
1 |
የተለያዩ የማሽን መለዋወጫ ዕቃዎች |
ዋና መሥሪያ ቤት |
DCE/SP/146/2025 |
ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም 8:15 ሰዓት |
ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም 8:30 ሰዓት |
50.000.00
|
ስለሆነም፡-
1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ ለተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ከሊራንስ) እና የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50.000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንከ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር በመከፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት አዲሱ ቢሮ ቃሊቲ ቶታል ስታዲየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ፡፡
5.ተጫራቶች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴከኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዥ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72 E-mail አድራሻ Info@dce-et.com
የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com
ቃሊቲ ቶታል ስታዲየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሱ ት/ቤት አጠገብ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
