የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የህንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ እና የተለያዩ የራስ እገዘ የልማት ፕሮጀክቶችን መገንባት ይፈልጋል። ገዳሙ ከመንፈሳዊ ተግባራት በተጨማሪ በአካባቢው ያለውን ማህበረሰብ የሚጠቅም አገልግሎት የሚሰጡ ግንባታዎችንም አካቷል።
በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተ-ክህነት ጽ/ቤት የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የህንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ እና የተለያዩ የራስ እገዘ የልማት ፕሮጀክቶችን መገንባት ይፈልጋል። ገዳሙ ከመንፈሳዊ ተግባራት በተጨማሪ በአካባቢው ያለውን ማህበረሰብ የሚጠቅም አገልግሎት የሚሰጡ ግንባታዎችንም አካቷል።
1. ተጫራቾች ከጨረታው መልስ ጋር የሚከተሉትን ሰነዶች ያቀርባሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/
- የግብር ግዴታ ለመወጣቱ ከሃገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠ ተጫራቹ የግብር ግዴታ የተወጣ በመሆኑ ጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችል የሚገልፅ የፅሁፍ ማስረጃ (ጊዜ ያላለፈበት መሆን ይኖርበታል)
- የተ.እ.ታክስ /NAT/ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣
- ተጫራቶች በታከስ ባለስልጣናት የተመዘገቡ እና የታከስ ማጽጃ ወረቀታቸውን ቅጂዎች ጨምሮ ትከከለኛ ሰነዶችን ማዘጋጀት መቻል አለባቸው፡፡
2. ተጫራቶች ሙት አንሣ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የግንባታ ሥራን ለማሰራት ቢያንስ GC 5.BC-5 እና ከዛ በላይ ህጋዊ የተመዘገበ ተቋራጭ መሆን አለባቸው።
3. ተጫራቾች የተናጠል ዋጋቸውን እና ጠቅላላ ዋጋቸውን ቫትን ጨምሮ በኢትዮጵያ ብር በግልጽ መግለጽ አለባቸው።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይያልተመሰረተ ባንከ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡ የኢንሹራንስ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፡፡
5. ተጫራቶች ጥያቄ ካላቸው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይሲሆን በአምስተኛው ቀን በ4፡00 ተዘግቶ በዛኑ ቀን በ5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የቴከኒካል እና የፋይናንሽያል ፕሮፖዛል በሁለት የተለያዩ ማህደሮች በማዘጋጅት ማስገባት ይችላሉ፡፡
8. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በታሸገ ቴክኒካል የጨረታ ሰነዱን ተጫራቾች ወይም ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የቴከኒክ ምዘናውን በተሳካ ሁኔታ ያለፈ ኮንትራከተርብቻ ለፋይናንስ ያለ ምዘና ግምት ውስጥ ይገባል። ቴክኒካል ብቁ የሆኑ ተጫራቾች የጨረታ መከፈቻው ዝርዝር መረጃ በመገኛ መረጃዎቻቸው ይነገራቸዋል።
9. የሙት አንሣ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር ሰነድ ከታች በተቀመጠው አድራሻ በአካል በመቅረብ ማስገባት ይችላሉ፡፡
አድራሻ፣ አዲስ አበባ መገናኛ ሾላ እልፍ ጸጋ ህንጻ 4ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-09-38-64-44-44/ 09-18-07-79-57
የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤስ አንድነት ገዳም
የህንጻ ቤተክርስቲያን
