በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ቋሚ ምድብ ችሎት የፍርድ ባለመብት የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት እና የፍርድ ባለዕዳ ፓውሎስ ዘለቀ ጠቅላላ ግንባታ ሥራ ተቋራጭ መካከል ባለው የፍርድ ማስፈጸሚያ ከርከርን አስመልክቶ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ምድብ ችሎት የፍርድ ባለዕዳ የሆኑት ንብረቶች፡
በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ቋሚ ምድብ ችሎት
የጨረታ ማስታወቂያ
የፍርድ ባለመብት የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት እና የፍርድ ባለዕዳ ፓውሎስ ዘለቀ ጠቅላላ ግንባታ ሥራ ተቋራጭ መካከል ባለው የፍርድ ማስፈጸሚያ ከርከርን አስመልክቶ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ምድብ ችሎት የፍርድ ባለዕዳ የሆኑት ንብረቶች፡
- የጭነት መኪና ታርጋ ቁጥር ET-03-37056 የሻንሲ ቁጥር LZGELBN 4778038034, የሞተር ቁጥር 150759342 የሆነ የመነሻ ዋጋ 1,500,000(አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) ሆኖ፣
- ዊል ሎደር ማሽን ሞዴል CLG 855 የሆነ የሻንሲ ቁጥር FT0800597 የሞተር ቁጥር 1508B030339 የሆነ የመነሻ ዋጋ ብር 4,500,000 (አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር)፣
- ፒካፕ መኪና ታርጋ ቁጥር AA-03-01-45813 የሻንሲ ቁጥር MAITX 4BKL72B67988 የሞተር ቁጥር BK74B16764 የሆነ የጨረታ መነሻ ዋጋ 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በሆነ በ01/03/2018 ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ጀምሮ እስከ 6፡00 ሰዓት ግልጽ ጨረታ በማካሄድ በከፍተኛ ዋጋ በሚያገኘው ሽጦ የጨረታ ውጤት ኅዳር 03/03/2018 ዓ.ም ከሰዓት በፊት 4፡00 ሰዓት እንዲቀርብ ታዟል። ስለዚህ መኪናዎች እና ዊል ሎደር ማሽኖች ከላይ የተገለጹት በጨረታው በመሳተፍ መግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትነ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ለጨረታ ለሚቀርቡ ንብረት መነሻ ጨረታ ዋጋ ከላይ የተገለጸውን 1/4ኛ በሲንቄ ባንክ ሲፒኦ (CPO) በማስያዝ ቀርቦ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለመመዝገብ በሚመጡበት ጊዜ መታወቂያ ይዞ መቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊ ተጫራች ቀሪው ገንዘብ ችሎት በሚሰጥበት ቀን ውስጥ አስገብቶ የሚያጠናቀቅ ሆኖ ጨረታውን ለማያሸንፉ ተጫራቾች የማስያዝያ ማስረጃ ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈትት ቦታ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የእሳት አደጋ መከላከያ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ከላይ በተገለጸው ሰዓት እና ቀን ነው።
- ተጫራቾች መኪናዎች እና ማሽኖች ለጨረታ የቀረቡት የመነሻ ዋጋቸው ብር ልዩነት ያለው ስለሆነ የምትፈልጉትን ለይታችሁ መወዳደር ትችላላችሁ። በዚሁ ሁኔታ ፍላጎት ያላችሁ ሁሉ የተቀመጠውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ቋሚ
ምድብ ችሎት
