በጋሞ ዞን የሰላምበር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቅ/ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የተለያዩ ማቴሪያሎች ግዥ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጋሞ ዞን የሰላምበር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በጋሞ ዞን የሰላምበር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቅ/ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የተለያዩ ማቴሪያሎች ግዥ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
የሕንፃ መሣሪያዎች፣
የጽሕፈት መሣሪያዎችና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
-ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
-ፈርኒቸር ዕቃዎች፣
-ጀኔሬተር አይነቶች፣
ስለሆነም በመንግሥት ገዢ ስዋጅና ደንብ መመሪያ መሠረት፡
1. የታደስ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
3. የግብር ከፋይነት ምዝገባ ቁጥር /Tin Number/ ያላቸው፣
4. ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና መረጃ ማያያዝ የሚችሉ፣
5. ከሽያጭ ዋጋ ላይ የመንግሥት ግብር 3% ለመከፈል ፈቃደኛ የሆኑ፣
6. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
7. የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
8. የጨረታው ሁኔታ በአይነትም /በጥቅል ሊሆን ይችላል፣
9. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴከኒካል ዋና እና ፋይናንሻል ዋና በመለየት በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማስገባት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ በሰ/በር/ከ/አ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ላይ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
10 በጨረታ ሂደት ላይ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ከጠቅላላው ዋጋ ላይ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለበት፤
11 ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይቀናት ይሆናል፡፡
12. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት በሰላምበር ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት የሚችሉ ይሆናል።
13. በጨረታ ለመሳተፍ በቅድሚያ በተዘረዘረው መሰረት የጨረታ ዋስትና የሚሆን ቢያንስ ለ120 ቀናት ፀንቶ ሚቆይ በCPO ወይም ባንክ ጋራንቲ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ጠቅላላ ዋጋ የያዘ የባንከ ማህተም በስተጀርባው የተቀመጠ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
14. የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው የጨረታው ማብቂያ በ21ኛው ቀን ከቀኑ11፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
15. ጨረታው የሚከፈተው በ22ኛው ቀን 3:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
16 በጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ወይም ግለሰብ ዕቃውን እስከ ሰላምበር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ የጫኚ እና አውራጅና የጭነት ወጪ በመሸፈን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
17.ተጫራቾች ወይም የተጫራቹ ወኪል አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
18.22ኛው ቀን ሰንበት ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ:- መ/ቤቱ ጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኝ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ሞባይል ቁጥር፡-09-84-68-97-47/ 09-55-32-50-04
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በጋሞ ዞን የሰላምበር ከተማ
አስተዳደር ፋይናንስ ቅ/ጽ/ቤት
