Tender Detail

Tender Details

  • Company በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ /ደ/ት/ቤት
  • Address ቀይ ኮከብ ቅደመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ልዩ ስሙ ጣሊያን ሰፈር ወይም ከዮሃንስ ቤተክርስትያን ወደ ጎጃም በረንዳ በሚወስደው መንገድ አራት መንታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-71-50-64
  • Website
  • Deadline20 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security10,000 (አስር ሺህ ብር) ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ
  • opening date2025-10-20 00:00:00
  • Categories Building Construction , Construction Works

ቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ሊያሰራው ለፈለገው ስራ የጥገና ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል።

በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ /ደ/ት/ቤት


 

የጥገና የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም

 

ቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ሊያሰራው ለፈለገው ስራ የጥገና ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ለግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን የሰው ሃይል በማቅረብ የሚሰሩ በጥቃቅን አነስተኛ ዘርፍ ማህበራት የተደረጁ ህጋዊ የሥራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል። ተቋራጮች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

 

ተ.ቁ

የስራው አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና

ደረጃ

የጨረታ ሰነዱ መሸጥ የሚጀመርበት ቀን

የጨረታ ማስገቢያ ቀን

የጨረታ መክፈቻ ቀን

1

የቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የጥገና ስራ

10,000 (አስር ሺህ ብር) ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ

በጥቃቅንና አነስተኛ ታዳጊ እና መብቃት

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት 2፡30-10፡30 ሰዓት

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30-4፡00 ሰዓት ድረስ

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን በ16ኛው የስራ ቀን ከ4፡30 ሰዓት ጀምሮ

 

ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ ዶክሜንታችሁን ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።

  1. በዘርፉ የ2017/2018ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ታከስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  3. ማንኛውም ስራ ተቋራጭ ከፌደራል ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ያላቸው እና ከአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ እና ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ተመዝግቦ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይዝ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ ቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 03 ቀርበው ሠነዱን 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  5. ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው የሥራ ቀን በእለቱ ባለቤቱና ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በት/ቤቱ ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል።
  6. ማንኛውም ተጫራቾች ለ60 ቀናት የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / BID BOND /በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቀይ ኮከብ ቅድመ በባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ (UnConditional Bank Guarantee) ከላይ በተጠቀሰው የብር መጠን ማቅረብ ግዴታ አለበት። የቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ያለበት በቴክኒካል ኦርጂናል ሰነድ ውስጥ ወይም ከፖስታው ውጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. አሰሪው መ/ቤት አሸናፊው ካሸነፈበት አጠቃላይ የስራ መጠን 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይቻላል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾችን መመሪያ (Instruction to Bidder (ITB) እንዲያነቡና የግንባታ ሳይቱን እንዲመለከቱ ይገደዳሉ።
  9. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ፣ ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ መቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የታሸገውን ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ ፕሮጀክት አይነት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። እንዲሁም የጨረታው ፋይናንሻል ሰነድ ላይ ያልተፈረመ ሆኖ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የተስተካከለ ዋጋ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ከጨረታው ያሰርዛል። በተጨማሪም በስራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የስራ አይተም ላይ ዋጋ አለመሙላት ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል።
  10. ተጫራቾች የሥራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ መወዳደሪያ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውን ማስፈር ማህተም ማድረግ ኢንቨሎፑን በማሸግ ማስታወቂያው በወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን የቀይ ኮኮብ ቅድመ እንደኛ፤ አንደኛ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ስራ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 08 በተዘጋጀ ውሳጥን ውስጥ እስከ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  11. ተጫራቾች ከዚህ በፊት ት/ቤቱ ባስገነባቸው ግንባታዎችም ሆነ እድሳቶች ምንም አይነት ውል ያላቋረጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
  12. አሸናፊ ተጫራች በስራ ዝርዝር ላይ ከገበያ ዋጋ በጣም ከፍ ያለ እና ዝቅ ያለ ዋጋ ከሞላ (Cost Break Down) ያቀርባል።
  13. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የድርጅቱ የስራ ልምድና ማንኛውም በቴክኒካል የተጠየቁት ዶክመንቶችን አሰሪ መ/ቤት ኦርጂናል ዶክመንት ከሰጠው አካል የማጣራት መብት የተጠበቀ ነው።
  14. ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ16ኛው ተከታታይ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ጀምሮ የቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ ፤ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ቁጥር 02 ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
  15. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ተጨማሪ ማብራሪያና አድራሻ፡- ቀይ ኮከብ ቅደመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ /ደ/ት/ቤት ልዩ ስሙ ጣሊያን ሰፈር ወይም ከዮሃንስ ቤተክርስትያን ወደ ጎጃም በረንዳ በሚወስደው መንገድ አራት መንታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

ለበለጠ መረጃ በት/ቤቱ ስልክ ቁጥር 011-1-71-50-64 ደውለው ይጠይቁ

 

በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ /ደ/ት/ቤት

 

 

Save Tender