በየካ ክ/ከ የወ01 ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት አመት በመንግስት ከተመደበለት ትሬዠሪና የውስጥ ገቢ መደበኛ በጀት በ1ኛ ዙር ብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች የተገለጹትን የተለያዩ መድሃኒቶችን ኬሚካል እና የላብራቶሪ ሬኤጀንቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የየካ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 01 ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
በየካ ክ/ከ የወ01 ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት አመት በመንግስት ከተመደበለት ትሬዠሪና የውስጥ ገቢ መደበኛ በጀት በ1ኛ ዙር ብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች የተገለጹትን የተለያዩ መድሃኒቶችን ኬሚካል እና የላብራቶሪ ሬኤጀንቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች፡-
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- በመድሃኒት ግዥ አቅራቢነት የተፈቀደበት ከምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ኤጀንሲ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ ከተቋሙ ግዥ ክፍል መውሰድ የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት እና ስም ፊርማና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በማድረግ ዋናውንና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ በተቋሙ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ብቻ በማሰራት ዋናውን/ኦርጅናል ከሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በይፋ ይከፈታል፡፡
- የውል ማስከበሪያ የአሸነፋችሁበትን አጠቃላይ የብር መጠን 10% ሲፒኦ ውል ስትገቡ ማስያዝ አለባችሁ።
- መድሃኒቶቹ እንዲሁም ፈኤጀንቶቹ በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት መቅረብ አለባቸው፣ ኤክስፓየርድ ዴት ለሚያስፈልጋቸው መድሃኒትም ሆነ ሬኤጀንቶቹ የተመረቱባቸውና ኤክስፓየርድ ጊዜያቸው በግልጽ የሚታይ መሆን አለበት፣ የአገልግሎት ጊዜያቸው ቢያንስ አንድ አመት እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፡፡
- ዋጋ ስትሞሉ አጠቃላይ የሞላችሁትን ዋጋ ድምር ማስቀመጥ ይጠበቅባችኋል
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ፈረንሳይ ወደ አርባ አንድ እየሱስ በሚያስገባው መንገድ ገባ ብሎ ከወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት አጠገብ፡፡
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ፡- 011-1-54-84-54/011-1-54-96-80
የካ ክ/ከ የወ01 ጤና ጣቢያ
